Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አስቴር 9:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ንጉሡም ንግሥት አስቴርን፣ “አይሁድ በሱሳ ግንብ ዐምስት መቶ ሰውና ዐሥሩን የሐማ ልጆች ገድለዋል፤ አጥፍተዋልም። በተቀሩት በንጉሡ አውራጃዎችስ ምን አድርገው ይሆን? አሁንስ የምትለምኚው ምንድን ነው? ይሰጥሻል፤ የምትጠይቂውስ ምንድን ነው? ይፈቀድልሻል” አላት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ንጉሡም ንግሥት አስቴርን “እነሆ አይሁድ መናገሻ ከተማ በሆነችው በሱሳ ብቻ እንኳ የገደሉአቸው ሰዎች ቊጥር ዐሥሩን የሃማንን ወንዶች ልጆች ጨምሮ አምስት መቶ ደርሶአል፤ በየሀገሩ የገደሉአቸውማ ከዚህ እጅግ ሳይበልጥ አይቀርም፤ ታዲያ፥ አሁን ከዚህ ሌላ ምን ትፈልጊያለሽ? ይፈጸምልሻል፤ የምትፈልጊውን ንገሪኝ ይሰጥሻል!” አላት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ንጉሡም ንግሥቲቱን አስቴርን፦ አይሁድ በሱሳ ግንብ አምስት መቶ ሰዎችንና አሥሩን የሐማ ልጆች ገደሉ አጠፉአቸውም፥ በቀሩትስ በንጉሡ አገሮች እንዴት አድርገው ይሆን! አሁንስ ልመናሽ ምንድር ነው? ይሰጥሻል፥ ሌላስ የምትሺው ምንድር ነው? ይደረጋል አላት።

参见章节 复制




አስቴር 9:12
6 交叉引用  

ከዚያም ንጉሡ፣ “ንግሥት አስቴር ሆይ፤ ለምን መጣሽ? ከእኔ የምትፈልጊውስ ምንድን ነው? እስከ መንግሥቴ እኩሌታ እንኳ ቢሆን ይሰጥሻል” አላት።


የወይን ጠጅ እየጠጡ ሳለ ንጉሡ ዳግመኛ አስቴርን፣ “እስኪ የምትፈልጊው ምንድን ነው? ይሰጥሻል፤ ደግሞስ የምትጠይቂው ምንድን ነው? እስከ መንግሥቴ እኩሌታ እንኳ ቢሆን ይፈቀድልሻል” አላት።


በሁለተኛውም ቀን የወይን ጠጅ እየጠጡ ሳለ፣ ንጉሡ እንደ ገና፣ “ንግሥት አስቴር ሆይ፤ የምትለምኚው ምንድን ነው? ይሰጥሻል፤ የምትጠይቂውስ ምንድን ነው? እስከ መንግሥቴ እኩሌታ እንኳ ቢሆን ይደረግልሻል” አላት።


በሱሳ ግንብ የተገደሉት ሰዎች ብዛት በዚያ ዕለት ለንጉሡ ተነገረው።


በሱሳ የሚኖሩ አይሁድ አዳር በተባለው ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን በአንድነት መጡ፤ በሱሳም ሦስት መቶ ሰዎች ገደሉ፤ በምርኮው ላይ ግን እጃቸውን አልዘረጉም።


አዛዡም የጕልማሳውን እጅ ይዞ ለብቻው ገለል በማድረግ፣ “ልትነግረኝ የምትፈልገው ምንድን ነው?” አለው።


跟着我们:

广告


广告