1 ስለዚህ ንጉሡና ሐማ ከንግሥት አስቴር ጋራ ለመጋበዝ ሄዱ፤
1 ስለዚህም ንጉሡና ሃማን ለሁለተኛ ጊዜ ከአስቴር ጋር ለመጋበዝ አብረው ሄዱ፤
1 ንጉሡና ሐማም ከንግሥቲቱ ከአስቴር ጋር ለመጠጣት መጡ።
መልእክተኞቹ በንጉሡ ትእዛዝ ተቻኵለው ወጡ፤ ዐዋጁም በሱሳ ግንብ ተላለፈ። ንጉሡና ሐማ ለመጠጣት ተቀመጡ፤ የሱሳ ከተማ ግን ግራ ተጋብታ ነበር።
በንጉሡ ዘንድ ሞገስ ካገኘሁና የምፈልገውን ሊሰጠኝና ልመናዬንም ሊፈጽምልኝ ንጉሡን ደስ ካሠኘው፣ ንጉሡና ሐማ በማዘጋጅላቸው ግብዣ ላይ ነገ ይገኙልኝ። ከዚያም እኔ ለንጉሡ ጥያቄ መልስ እሰጣለሁ።”
ከርሱ ጋራ በመነጋገር ላይ ሳሉ፣ የንጉሡ ጃንደረቦች ደርሰው ሐማን አስቴር ወዳዘጋጀችው ግብዣ አጣደፉት።
በሁለተኛውም ቀን የወይን ጠጅ እየጠጡ ሳለ፣ ንጉሡ እንደ ገና፣ “ንግሥት አስቴር ሆይ፤ የምትለምኚው ምንድን ነው? ይሰጥሻል፤ የምትጠይቂውስ ምንድን ነው? እስከ መንግሥቴ እኩሌታ እንኳ ቢሆን ይደረግልሻል” አላት።