አስቴር 6:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ስለዚህ ሐማ ልብሱንና ፈረሱን ወስዶ መርዶክዮስን አለበሰው፤ በዋና ዋና መንገዶች ላይ እየመራም፣ “ንጉሥ ሊያከብረው ለሚወድደው ሰው ይህ ተደርጎለታል” እያለ በፊቱ ያውጅ ነበር። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ስለዚህም ሃማን ልብሰ መንግሥትና ፈረስ አዘጋጅቶ መርዶክዮስን አለበሰው፤ መርዶክዮስ በፈረሱ ላይ ከተቀመጠም በኋላ ሃማን ፊት ፊት እየሄደ በመምራት “ንጉሡ ሊያከብረው የፈለገውን ሰው እንዴት እንደ ሸለመው ተመልከቱ!” እያለ ያውጅ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ሐማም ልብሱንና ፈረሱን ወሰደ፥ መርዶክዮስንም አለበሰው፥ በፈረሱም ላይ አስቀመጠው፥ በከተማይቱም አደባባይ በፊቱ አሳለፈው። በፊቱም፦ ንጉሡ ያከብረው ዘንድ ለሚወድደው ሰው እንዲህ ይደረግለታል ብሎ አዋጅ ነገረ። 参见章节 |