አስቴር 5:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ሚስቱ ዞሳራና ወዳጆቹ በሙሉ፣ “ቁመቱ ዐምሳ ክንድ የሆነ መስቀያ አስተክልና መርዶክዮስ እንዲሰቀልበት በጧት ለንጉሡ ንገረው፤ ከዚያም ደስ ብሎህ ከንጉሡ ጋራ ወደ ግብዣው ግባ” አሉት። ይህም ሐሳብ ሐማን እጅግ ደስ አሠኘው፤ መስቀያውንም አስተከለ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ስለዚህ ሚስቱና ወዳጆቹ ሁሉ “ርዝመቱ ኻያ ሁለት ሜትር የሆነ መስቀያ እንጨት አዘጋጅተህ ነገ ጠዋት መርዶክዮስን ለመስቀል የንጉሡን ፈቃድ መጠየቅ ትችላለህ፤ ከዚያም በኋላ ደስ ብሎህ ወደ ግብዣው ትሄዳለህ” ሲሉ ሐሳብ አቀረቡለት። ሃማንም ሐሳቡ መልካም እንደ ሆነ ተቀብሎ የመስቀያውን እንጨት አዘጋጀ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ሚስቱም ዞሳራና ወዳጆቹ ሁሉ፦ ቁመቱ አምሳ ክንድ የሆነ ግንድ ይደረግ፥ ነገም መርዶክዮስ ይሰቀልበት ዘንድ ለንጉሡ ተናገር፥ ደስም ብሎህ ከንጉሡ ጋር ወደ ግብዣው ግባ አሉት። ነገራቸውም ሐማን ደስ አሰኘው፥ ግንዱንም አስደረገ። 参见章节 |