አስቴር 3:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም13 አዳር በተባለው በዐሥራ ሁለተኛው ወር፣ በዐሥራ ሦስተኛው ቀን ወጣት፣ ሽማግሌ፣ ሴትና ሕፃን ሳይባል አይሁድ ሁሉ በዚያ ዕለት እንዲጠፉ፣ እንዲገደሉና እንዲደመሰሱ፣ ሀብታቸውም እንዲዘረፍ ደብዳቤ ለንጉሡ አውራጃዎች ሁሉ በመልእክተኞች እጅ ተላከ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ፈጣኖች የሆኑ ሯጮችም ይህን ዐዋጅ በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ወደሚገኙት አገሮች ሁሉ እንዲያደርሱ ተላኩ፤ በዐዋጁም ውስጥ አዳር ተብሎ በሚጠራው በዐሥራ ሁለተኛው ወር፥ በዐሥራ ሦስተኛው ቀን መላውን የአይሁድ ወጣት፥ ሽማግሌ፥ ሴት፥ ወንድ ሳይቀር ሕፃናትንም ጭምር እንዲገድሉ፥ እንዲያጠፉና እንዲደመሰሱ የሚያዝ ቃል ነበረበት፤ ንብረታቸውም ሁሉ እንዲዘረፍ ትእዛዝ ወጥቶ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 በአሥራ ሁለተኛው ወር በአዳር በአሥራ ሦስተኛው ቀን አይሁድን ሁሉ፥ ልጆችንና ሽማግሌዎችን፥ ሕፃናቶችንና ሴቶችን፥ በአንድ ቀን ያጠፉና ይገድሉ ዘንድ፥ ይደመስሱም ዘንድ፥ ምርኮአቸውንም ይዘርፉ ዘንድ ደብዳቤዎች በመልእክተኞች እጅ ወደ ንጉሡ አገሮች ሁሉ ተላኩ። 参见章节 |