አስቴር 3:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም12 ከዚያም በመጀመሪያው ወር ዐሥራ ሦስተኛው ቀን የንጉሡ ጸሓፊዎች ተጠሩ። እነርሱም የሐማን ትእዛዝ በሙሉ በየአውራጃው ፊደልና በየሕዝቡ ቋንቋ፣ ለንጉሡ እንደራሴዎች፣ ለልዩ ልዩ አውራጃ ገዦችና ለልዩ ልዩ ሕዝቦች መኳንንት ጻፉ። ይህም የተጻፈው በራሱ በንጉሡ ጠረክሲስ ስም ሲሆን፣ የታተመውም በራሱ ማኅተም ነበር። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ስለዚህ የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ ሦስተኛው ቀን ሃማን የንጉሡን ጸሐፊዎች ጠርቶ ዐዋጁ በልዩ ልዩ ቋንቋዎች ተተርጒሞ፥ በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት በሚገኘው የአጻጻፍ ሥርዓት ሁሉ በመዘጋጀት፥ ወደ አገረ ገዢዎችና ወደ ባለሥልጣኖች ሁሉ እንዲላክ ያደርጉ ዘንድ አዘዘ፤ ዐዋጁም በንጉሥ አርጤክስስ ስም ተጽፎ የቀለበቱ ማኅተም ተደርጎበት ተላለፈ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 በመጀመሪያውም ወር ከወሩም በአሥራ ሦስተኛው ቀን የንጉሡ ጸሐፊዎች ተጠሩ፥ ከህንድ ጀምሮ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ ወዳሉ መቶ ሀያ ሰባት አገሮች፥ በየአገሩ ወዳሉ ሹማምትና አለቆች ወደ አሕዛብም ሁሉ ገዢዎች እንደ ቋንቋቸው በንጉሡ በአርጤክስስ ቃል ሐማ እንዳዘዘ ተጻፈ፥ በንጉሡም ቀለበት ታተመ። 参见章节 |