Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አስቴር 2:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ሲመሽ ወደዚያው ትሄዳለች፤ ሲነጋም የቁባቶች ኀላፊ በሆነው በንጉሡ ጃንደረባ በሻአሽጋዝ ጥበቃ ሥር ወደሚገኘው ወደ ሌላው የሴቶች መጠበቂያ ቤት ትመለሳለች፤ ደስ የተሠኘባት ካልሆነችና በስሟም ካልጠራት ዳግመኛ ወደ ንጉሡ ዘንድ አትገባም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እርስዋም ሌሊቱን ከንጉሡ ጋር ዐድራ በማግስቱ ወደ ሌላ የምርጥ ሴቶች መኖሪያ ቤት ትወሰዳለች፤ እዚያም የንጉሡ ቊባቶች ኀላፊ በሆነው በጃንደረባው በሻዕሸጋዝ ቊጥጥር ሥር ትሆናለች፤ በንጉሡ ዘንድ ተወዳጅነትን አግኝታ እርሱ ስምዋን ጠርቶ እንደገና እንድትመጣለት ካልጠየቀ በቀር ዳግመኛ ወደ እርሱ አትቀርብም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ማታም ትገባ ነበር፥ ሲነጋም ተመልሳ ወደ ሁለተኛው ሴቶች ቤት ቁባቶችን ወደሚጠብቅ ወደ ንጉሡ ጃንደረባ ወደ ጋይ ትመጣ ነበር፥ ንጉሡም ያልፈለጋት እንደ ሆነ፥ በስምዋም ያልተጠራች እንደሆነ፥ ከዚያ ወዲያ ወደ ንጉሡ አትገባም ነበር።

参见章节 复制




አስቴር 2:14
8 交叉引用  

ከአባቱ ቤተ ሰብ ሁሉ እጅግ የተከበረው ይህ ወጣት የያዕቆብን ልጅ እጅግ ወድዷት ስለ ነበር፣ ያሉትን ለማድረግ ጊዜ አልወሰደበትም።


ወደ ንጉሡ ዘንድ የምትገባውም በዚህ ሁኔታ ሲሆን፣ ሴቶቹ ከሚኖሩበት ስፍራ ወደ ንጉሡ ቤተ መንግሥት ስትሄድ፣ መውሰድ የምትፈልገው ማንኛውም ነገር ይሰጣት ነበር።


መርዶክዮስ እንደ ልጁ አድርጎ ያሳደጋት የአጎቱ የአቢካኢል ልጅ አስቴር ወደ ንጉሡ ዘንድ የምትሄድበት ተራ በደረሰ ጊዜ የሴቶች ልዩ ጥበቃ ቤት ኀላፊ የሆነው ሄጌ የነገራትን እንጂ፣ ሌላ ምንም አልጠየቀችም። አስቴር በሚያዩዋት ሁሉ ዘንድ ሞገስ አገኘች።


“የንጉሡ ባሮችና በንጉሡ አውራጃዎች የሚገኙ ሰዎች ሁሉ ወንድም ሆነ ሴት፣ ማንም ሰው ሳይጠራ ንጉሡ ወዳለበት ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚገባ፣ ንጉሡ አንድ ሕግ ብቻ እንዳለው ያውቃል፤ ይኸውም እንዲህ ያደረገው ሰው ይገደላል፤ አንድ ሰው ከእንዲህ ዐይነቱ ሞት የሚተርፈው፣ ንጉሡ የወርቅ ዘንጉን ሲዘረጋለት ብቻ ነው። እኔ ግን ወደ ንጉሡ ዘንድ እንድገባ ከተጠራሁ ከሠላሳ ቀን በላይ ሆነ።”


አሁን ግን፣ ያዕቆብ ሆይ የፈጠረህ፣ እስራኤል ሆይ! የሠራህ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ፤


ስለ ባሪያዬ ስለ ያዕቆብ፣ ስለ መረጥሁት ስለ እስራኤል፣ አንተ ባታውቀኝ እንኳ፣ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ የክብርም ስም ሰጥቼሃለሁ።


በርሷ ደስተኛ ባትሆን፣ ወደምትፈልገው እንድትሄድ ነጻነት ስጣት፤ ውርደት ላይ ጥለሃታልና ልትሸጣት ወይም እንደ ባሪያ ልትቈጥራት አይገባህም።


跟着我们:

广告


广告