Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መክብብ 8:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 አምላክ ያደረገውን ሁሉ አየሁ። ከፀሓይ በታች የሚደረገውን ማንም ሊያውቅ አይችልም፤ ሰው ለመመርመር ብዙ ቢጥርም፣ ትርጕሙን ማግኘት አይችልም፤ ጠቢብም እንኳ ዐውቀዋለሁ ቢል፣ ፈጽሞ ሊገነዘበው አይችልም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የእግዚአብሔርንም ሥራ ሁሉ አየሁ፤ እርሱም ከፀሐይም በታች የተደረገውን ሥራ መርምሮ ሰው ማግኘት አለመቻሉን፥ ሰውም በመፈለግ እጅግ ቢደክምም መርምሮ አለማግኘቱን ነው፥ ደግሞም ጠቢብ ሰው አውቀዋለሁ ቢልም እንኳን ይህንን ለማግኘት አይችልም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ሰው በምርምር ብዛትም እግዚአብሔር የሚያደርገውን ነገር ሁሉ ማወቅ እንደማይችል አረጋገጥኩ፤ ሰው ብዙ ነገር መርምሮ ለማወቅ የቱንም ያኽል ቢደክም አንዳች ነገር ማግኘት አይችልም፤ በእርግጥ ጥበበኞች ሰዎች “ይህንን እናውቃለን” ለማለት ይደፍሩ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ የሚያውቁት ነገር የለም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ከፀ​ሓ​ይም በታች የተ​ደ​ረ​ገ​ውን ሥራ መር​ምሮ ያገኝ ዘንድ ለሰው እን​ዳ​ይ​ቻ​ለው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ሁሉ አየሁ። ሰውም ሊፈ​ልግ እጅግ ቢደ​ክም መር​ምሮ አያ​ገ​ኘ​ውም፤ ደግ​ሞም ጠቢብ ሰው፥ “ይህን ዐወ​ቅሁ” ቢል እርሱ ያገ​ኘው ዘንድ አይ​ች​ልም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ከፀሐይም በታች የተደረገውን ሥራ መርምሮ ያገኝ ዘንድ ለሰው እንዳይቻለው የእግዚአብሔርን ሥራ ሁሉ አየሁ። ሰውም ሊፈልግ እጅግ ቢደክም መርምሮ አያገኘውም፥ ደግሞ ጠቢብ ሰው፦ ይህን አወቅሁ ቢል እርሱ ያገኘው ዘንድ አይችልም።

参见章节 复制




መክብብ 8:17
13 交叉引用  

እርሱ፣ የማይመረመሩ ድንቅ ነገሮች፣ የማይቈጠሩም ታምራት ያደርጋል።


እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህ እንዴት ብዙ ነው! ሁሉን በጥበብ ሠራህ፤ ምድርም በፍጥረትህ ተሞላች።


እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ አንተ ያደረግኸው ድንቅ ነገር ብዙ ነው፤ ለእኛ ያቀድኸውን፣ ሊዘረዝርልህ የሚችል ማንም የለም፤ ላውራው ልናገረው ብል፣ ስፍር ቍጥር አይኖረውም።


ይህን ነገር ለመረዳት በሞከርሁ ጊዜ፣ አድካሚ ተግባር መስሎ ታየኝ።


ከሰማይ በታች የተደረገውን ሁሉ በጥበብ ለማጥናትና ለመመርመር ራሴን አተጋሁ፤ አምላክ በሰዎች ላይ የጫነው እንዴት ያለ ከባድ ሸክም ነው!


የነፋስን መንገድ እንደማታውቅ፣ ሕይወት ወይም መንፈስ በእናት ማሕፀን ውስጥ ወደሚገኘው አካል እንዴት እንደሚገባም እንደማታውቅ ሁሉ፣ ሁሉን ሠሪ የሆነውን፣ የአምላክን ሥራ ማስተዋል አትችልም።


ሁሉንም ነገር በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፤ በሰዎችም ልብ ዘላለማዊነትን አኖረ፤ ይሁን እንጂ አምላክ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ያደረገውን ማወቅ አይችሉም።


አምላክ ያደረገውን ተመልከት፤ እርሱ ያጣመመውን፣ ማን ሊያቃናው ይችላል?


አታውቅምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፣ የምድር ዳርቻ ፈጣሪ ነው። አይደክምም፤ አይታክትም፤ ማስተዋሉም በማንም አይመረመርም።


የእግዚአብሔር የጥበቡና የዕውቀቱ ባለጠግነት እንዴት ጥልቅ ነው! ፍርዱ አይመረመርም፤ ለመንገዱም ፈለግ የለውም!


跟着我们:

广告


广告