Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መክብብ 8:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በወንጀል ላይ ባፋጣኝ ፍርድ ካልተሰጠ፣ የሰዎች ልብ ክፉን በማድረግ ዕቅድ ይሞላል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በክፉ ሥራ ላይ ፈጥኖ ፍርድ አይበየንምና በሰው ልጆች ልብ ውስጥ ክፉን መሥራት ጠነከረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ሰዎች ሆን ብለው ወንጀል የሚሠሩት ለምንድን ነው? የዚህ ምክንያት ሌላ ሳይሆን ወንጀል በሚሠሩ ሰዎች ላይ ፈጣን የቅጣት ፍርድ ባለመሰጠቱ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ክፉን ከሚ​ያ​ደ​ርጉ ወገን ፈጥኖ ክር​ክ​ርን የሚ​ያ​ደ​ርግ የለ​ምና፤ ስለ​ዚህ የሰው ልጆች ልብ በእ​ነ​ርሱ ክፉን ለመ​ሥ​ራት ጠነ​ከረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በክፉ ሥራ ላይ ፈጥኖ ፍርድ አይፈረድምና ስለዚህ በሰው ልጆች ውስጥ ልባቸው ክፉን ለመሥራት ጠነከረ።

参见章节 复制




መክብብ 8:11
19 交叉引用  

በደብዳቤውም ላይ፣ “ኦርዮ ውጊያው በተፋፋመበት ግንባር መድበው፤ ከዚያም ተወግቶ እንዲሞት ትታችሁት ሽሹ” ብሎ ጻፈ።


ያለ ሥጋት እንዲኖሩ ትቷቸው ይሆናል፤ ዐይኖቹ ግን በመንገዳቸው ላይ ናቸው።


ክፉ ሰው ከትዕቢቱ የተነሣ እግዚአብሔርን አይፈልግም፤ በሐሳቡም ሁሉ አምላክ የለም፤


በልቡም፣ “ከስፍራዬ የሚነቀንቀኝ የለም፤ ከትውልድ እስከ ትውልድም መከራ አያገኘኝም” ይላል።


ጌታ ሆይ፤ አንተ ግን መሓሪና ርኅሩኅ አምላክ ነህ፤ ለቍጣ የዘገየህ፣ ምሕረትህና ታማኝነትህ የበዛ።


እርሱም በሙሴ ፊት እንዲህ እያለ እያወጀ ዐለፈ፤ “እግዚአብሔር ርኅሩኅና ቸር አምላክ፣ እግዚአብሔር ለቍጣ የዘገየ፣ ፍቅሩና ታማኝነቱ የበዛ፣


ፈርዖን ችግሩ ጋብ ማለቱን ባየ ጊዜ ግን ልክ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው ልቡን በማደንደን ሙሴንና አሮንን አልሰማቸውም።


በዚህም ጊዜ እንኳ ፈርዖን ልቡን አደነደነ እንጂ፣ ሕዝቡን አልለቀቀም።


ከፀሓይ በታች በሁሉም ላይ የሚሆነው ክፋት ይህ ነው፤ የሁሉም የመጨረሻ ዕጣ ፈንታ አንድ ነው። በዚህም ላይ የሰዎች ልብ በክፋት የተሞላ ነው፤ በሕይወት እያሉም በልባቸው ውስጥ እብደት አለ፤ በመጨረሻም ወደ ሙታን ይወርዳሉ።


ክፉዎች ርኅራኄ ቢደረግላቸው እንኳ፣ ጽድቅን አይማሩም፤ በቅንነት ምድር እንኳ ክፋትን ያደርጋሉ፤ የእግዚአብሔርንም ግርማ አያስተውሉም።


“እኔን የዋሸሽኝ፤ ማንን ፈርተሽ፣ ማንንስ ሠግተሽ ነው? እኔን ያላስታወስሽው፣ ይህንም በልብሽ ያላኖርሽው፣ እኔን ያልፈራሽው፣ ዝም ስላልሁ አይደለምን?


እንግዲህ የይሁዳ ቅሬታ ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ወደ ግብጽ ለመሄድ ወስናችሁ እዚያ ለመቀመጥ ብትሄዱ፣


“ሞዓብ በአንቡላው ላይ እንዳረፈ የወይን ጠጅ፣ ከልጅነት ጀምሮ የተረጋጋ ነበረ፤ ከዕቃ ወደ ዕቃ አልተገላበጠም፤ በምርኮም አልተወሰደም፤ ቃናው እንዳለ ነው፤ መዐዛውም አልተለወጠም።


跟着我们:

广告


广告