Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መክብብ 1:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ማንም፣ “እነሆ፤ ይህ አዲስ ነገር ነው!” ሊል የሚችለው አንዳች ነገር አለን? ቀድሞውኑ በዚሁ የነበረ ነው፤ ከእኛ በፊት የሆነ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ማንም፦ እነሆ፥ ይህ ነገር አዲስ ነው ማለት ይችላልን? እርሱ ከእኛ በፊት በነበሩት ዘመናት ተደርጎአል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ማንም ሰው “እነሆ ይህ አዲስ ነገር ነው!” ቢል ያ ነገር እኛ ከመወለዳችን አስቀድሞ የነበረ ሆኖ ይገኛል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እነሆ፥ “ይህ ነገር አዲስ ነው” ብሎ የሚ​ና​ገር ማን ነው? እርሱ ከእኛ በፊት በነ​በ​ሩት ዘመ​ናት ተደ​ር​ጓል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ማንም፦ እነሆ፥ ይህ ነገር አዲስ ነው ይል ዘንድ ይችላልን? እርሱ ከእኛ በፊት በነበሩት ዘመናት ተደርጎአል።

参见章节 复制




መክብብ 1:10
10 交叉引用  

የቀድሞ ነገሮች መታሰቢያ የላቸውም፤ ወደ ፊት የሚመጡትም ቢሆኑ፣ ከእነርሱ በኋላ በሚተኩት አይታወሱም።


የነበረው ነገር እንደ ገና ይሆናል፤ የተደረገውም ተመልሶ ይደረጋል፤ ከፀሓይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም።


ከዚያም ጥበብን፣ እብደትንና ሞኝነትን ለመመርመር ሐሳቤን መለስሁ፤ አስቀድሞ ከተደረገው በቀር፣ ከንጉሥ በኋላ የሚመጣው ሰው ምን ሊያደርግ ይችላል?


አሁን ያለው ሁሉ አስቀድሞ ስም የተሰጠው ነው፤ ሰው የሚሆነውም አስቀድሞ የታወቀ ነው፤ ከራሱ ይልቅ ከሚበረታ ጋራ፣ ማንም አይታገልም።


በሰማይ የምትቀበሉት ዋጋ ታላቅ ስለ ሆነ ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያት እንደዚሁ አሳድደዋቸዋልና።


“እናንተ ልባችሁና ጆሯችሁ ያልተገረዘ! ዐንገተ ደንዳኖች ልክ እንደ አባቶቻችሁ መንፈስ ቅዱስን ሁልጊዜ ትቃወማላችሁ።


ኢያኔስና ኢያንበሬስ ሙሴን እንደ ተቃወሙት፣ እነዚህ አእምሯቸው የጠፋባቸውና ከእምነት የተጣሉ ሰዎች ደግሞ እውነትን ይቃወማሉ።


跟着我们:

广告


广告