ዘዳግም 9:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም9 እኔም የድንጋይ ጽላቱን፣ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ የገባውን የኪዳን ጽላት ለመቀበል ወደ ተራራው በወጣሁ ጊዜ፣ እህል ሳልበላ፣ ውሃም ሳልጠጣ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቈየሁ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 የድንጋዩን ጽላቶች፥ ጌታ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን የፈጸመባቸውን ጽላቶች፥ ለመቀበል ወደ ተራራ በወጣሁ ጊዜ፥ በተራራው አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ተቀምጬ ነበር፤ እህል አልቀመስኩም፥ ውኃም አልጠጣሁም። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የገባው ቃል ኪዳን የተጻፈባቸውን የድንጋይ ጽላቶች ለመቀበል እኔ ወደ ተራራው ወጥቼ ነበር፤ በዚያም ምንም ነገር ሳልበላና ሳልጠጣ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቈየሁ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ሁለቱን የድንጋይ ጽላት፥ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የተማማለባቸውን የቃል ኪዳን ጽላት እቀበል ዘንድ ወደ ተራራ በወጣሁ ጊዜ፥ በተራራው አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ተቀምጬ ነበር፤ እንጀራ አልበላሁም፤ ውኃም አልጠጣሁም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 የድንጋዩን ጽላቶች፥ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የተማማለባቸውን የቃል ኪዳን ጽላቶች፥ እቀበል ዘንድ ወደ ተራራ በወጣሁ ጊዜ፥ በተራራው አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ተቀምጬ ነበር፤ እንጀራ አልበላሁም፥ ውኃም አልጠጣሁም። 参见章节 |