ዘዳግም 5:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም28 ይህን ስትነግሩኝ እግዚአብሔር ሰማ፤ እግዚአብሔርም አለኝ፤ “ይህ ሕዝብ ምን እንዳለህ ሰምቻለሁ፤ ያሉትም ሁሉ መልካም ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)28 “በተናገራችሁኝም ጊዜ ጌታ የእናንተን ቃል ጽምፅ ሰማ፤ ጌታም አለኝ፦ ‘የዚህን ሕዝብ ነገር፥ የተናገሩህን ቃል ድምፅ ሰምቼአለሁ፤ የተናገሩህ ሁሉ መልካም ነው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም28 “እግዚአብሔርም፥ ይህን ስትሉኝ በሰማ ጊዜ እንዲህ አለኝ፤ ‘እነዚህ ሰዎች ለአንተ የተናገሩትን ሁሉ ሰምቻለሁ፤ አባባላቸውም ትክክል ነው፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)28 “በተናገራችሁኝም ጊዜ እግዚአብሔር የእናንተን ቃል ድምፅ ሰማ፤ እግዚአብሔርም አለኝ፦ ይህ ሕዝብ የተናገሩህን ቃል ድምፅ ሰምቼአለሁ፤ የተናገሩህ ሁሉ ትክክል ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)28 በተናገራችሁኝም ጊዜ እግዚአብሔር የእናንተን ቃል ጽምፅ ሰማ፤ እግዚአብሔርም አለኝ፦ ይህ ሕዝብ የተናገሩህን ቃል ድምፅ ሰምቼአለሁ፤ የተናገሩህ ሁሉ መልካም ነገር ነው። 参见章节 |