Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 4:43 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 ከተሞቹም በምድረ በዳው በከፍተኛ ቦታ ላይ የምትገኘው ቦሶር ለሮቤላውያን፣ በገለዓድ የምትገኘው ራሞት ለጋዳውያን፣ በባሳን ያለችው ጎላን ለምናሴያውያን ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 ከተሞቹም ለሮቤል ነገድ በምድረ በዳ በደልዳላ ስፍራ ያለ ቤጼር፥ ለጋድም ነገድ በገለዓድ ያለ ራሞት፥ ለምናሴም ነገድ በባሳን ያለ ጎላን ነበሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 ስለዚህም ለሮቤል ነገድ ከፍታ ባለው በረሓ የምትገኘው የቤጼር ከተማ፥ ለጋድ ነገድ በገለዓድ ግዛት የምትገኘው ራሞትና፥ ለምናሴም ነገድ በባሳን ግዛት ውስጥ የምትገኘው ጎላን እንዲለዩ አደረገ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 ለሮ​ቤል ነገድ በም​ድረ በዳ በደ​ል​ዳላ ስፍራ ያለ ባሶር፥ ለጋ​ድም ነገድ በገ​ለ​ዓድ ያለ ራሞት፥ ለም​ና​ሴም ነገድ በባ​ሳን ያለ ጎላን ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 ከተሞቹም ለሮቤል ነገድ በምድረ በዳ በደልዳላ ስፍራ ያለ ቦሶር፥ ለጋድም ነገድ በገለዓድ ያለ ራሞት፥ ለምናሴም ነገድ በባሳን ያለ ጎላን ነበሩ።

参见章节 复制




ዘዳግም 4:43
12 交叉引用  

ቤንጌበር፣ በገለዓድ ራሞት ከተማ እዚያው ገለዓድ ውስጥ የምናሴ ልጅ የኢያዕር መንደሮች፣ በባሳንም የአርጎብ አውራጃ እንዲሁም በሮቻቸው የናስ መወርወሪያ በሆኑ ስድሳ ባለ ቅጥር ታላላቅ ከተሞች፤


ለሜራሪ ዘሮች በየጐሣቸው ከሮቤል፣ ከጋድና ከዛብሎን ድርሻ ላይ ዐሥራ ሁለት ከተሞች ተመደቡላቸው።


ለአንዳንድ የቀዓት ጐሣዎችም ከኤፍሬም ነገድ ድርሻ ላይ የሚኖሩበት ከተማ ተሰጣቸው።


ጌርሶናውያን ከዚህ የሚከተሉትን ከተሞች ወሰዱ፤ ከምናሴ ነገድ እኩሌታ፣ በባሳን የሚገኘውን ጎላንና አስታሮትን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤


ከጋድ ነገድ በገለዓድ የምትገኘውን ራሞትን፣ መሃናይምን፣


ይኸውም የቈየ ጠላትነት ሳይኖር፣ በድንገት ባልንጀራውን የገደለ ማንኛውም ሰው ሸሽቶ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ በመሄድ ሕይወቱን ማትረፍ ይችል ዘንድ ነው።


ሙሴ በእስራኤላውያን ፊት የደነገገው ሕግ ይህ ነው።


እንደዚሁም ከዮርዳኖስ ማዶ ከኢያሪኮ በስተምሥራቅ በሮቤል ነገድ ይዞታ ውስጥ ከፍታ ባለው ምድረ በዳ ያለችውን ቦሶርን፣ በጋድ ነገድ ይዞታ ውስጥ ባለችው በገለዓድ የምትገኘውን ራሞትንና በምናሴ ነገድ ይዞታ ውስጥ በባሳን የምትገኘውን ጎላንን ለዩ።


የጌርሶን ወገኖች ለሆኑት ለሌሎቹ የሌዊ ጐሣዎች የተሰጧቸው የሚከተሉት ናቸው፤ ከምናሴ ነገድ እኩሌታ፣ በባሳን ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ የሆነችው ከተማ ጎላንና በኤሽትራ እነዚህ ሁለት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤


ከሮቤል ነገድ፣ ቦሶር፣ ያሀጽ፣


ከጋድ ነገድ፣ በገለዓድ ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ የሆነችው ከተማ ራሞት መሃናይም፣


跟着我们:

广告


广告