Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 32:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 አእምሮ የጐደላቸው፣ ማስተዋልም የሌላቸው ሕዝብ ናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 “ምክር ያጡ ሕዝብ ናቸው፥ ማስተዋልም የሌላቸው ናቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 “የእስራኤል ሕዝብ አእምሮ ቢሶች ናቸው፤ አያስተውሉምም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ምክር ያጡ ሕዝብ ናቸው፤ ምግ​ባ​ርና ሃይ​ማ​ኖት የላ​ቸ​ውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ምክር ያጡ ሕዝብ ናቸው፥ 2 ማስተዋልም የላቸውም።

参见章节 复制




ዘዳግም 32:28
12 交叉引用  

ከዚያም ሰውን፣ ‘እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ ከክፋትም መራቅ ማስተዋል ነው’ አለው።”


ስለዚህ በገዛ ዕቅዳቸው እንዲሄዱ፣ አሳልፌ ለደንዳናው ልባቸው ሰጠኋቸው።


እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት መጀመሪያ ነው፤ ቂሎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።


ጫፎቿ ሲደርቁ ይሰበራሉ፤ ሴቶችም መጥተው ይማግዷቸዋል። ማስተዋል የሌለው ሕዝብ ስለ ሆነ፣ ፈጣሪው አይራራለትም፤ ያበጀውም አይምረውም።


ስለዚህ ይህን ሕዝብ በድንቅ ላይ ድንቅ ነገር እያደረግሁ፣ ዳግመኛ አስገርመዋለሁ፤ የጥበበኞችን ጥበብ አጠፋለሁ፤ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትሰወራለች።”


“ሕዝቤ ቂሎች ናቸው፤ እኔን አያውቁኝም። ማስተዋል የጐደላቸው፣ መረዳትም የማይችሉ ልጆች ናቸው። ክፋትን ለማድረግ ጥበበኞች፣ መልካም መሥራት ግን የማያውቁ።”


ጥበበኞች ያፍራሉ፤ ይዋረዳሉ፤ በወጥመድም ይያዛሉ። የእግዚአብሔርን ቃል ተቃውመው፣ ምን ዐይነት ጥበብ ይኖራቸዋል?


ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቷል። ዕውቀትን ስለ ናቃችሁ፣ እኔም ካህናት እንዳትሆኑ ናቅኋችሁ፤ የአምላካችሁን ሕግ ስለ ረሳችሁ፣ እኔም ልጆቻችሁን እረሳለሁ።


ወንድሞች ሆይ፤ ልባሞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ፣ ይህን ምስጢር ሳታውቁ እንድትቀሩ አልፈልግም፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ እስራኤል በከፊል በድንዳኔ ውስጥ ዐልፋለች።


የዚህ ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ፊት ሞኝነት ነውና፤ እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፤ “እርሱ ጥበበኞችን በራሳቸው ተንኰል ይይዛቸዋል፤”


አንተ ሞኝና ጥበብ የጐደለህ ሕዝብ፣ ለእግዚአብሔር የምትመልስለት በዚህ መንገድ ነውን? አባትህ ፈጣሪህ፣ የሠራህና ያበጀህ እርሱ አይደለምን?


跟着我们:

广告


广告