Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 31:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ብዙ ጥፋትና የከፋ ችግር በደረሰባቸው ጊዜ ይህ መዝሙር ምስክር ይሆንባቸዋል፤ በዘሮቻቸው የሚረሳ አይደለምና። ወደ ማልሁላቸው ምድር ሳላስገባቸው በፊት ምን ለማድረግ እንደሚያስቡ እንኳ አስቀድሜ ዐውቃለሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ብዙ ጥፋትና የከፋ ችግር በደረሰባቸው ጊዜ ይህ መዝሙር ምስክር ይሆንባቸዋል። በዘራቸው የሚረሳ አይደለምና። ወደ ማልሁላቸው ምድር ሳላስገ ባቸው በፊት ምን ለማድረግ እንደሚያስቡ እንኳን አስቀድሜ ዐውቃለሁ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ብዙ ከባድ ችግሮች ሲደርሱባቸው ይህ በልጆቻቸው የማይረሳ መዝሙር ሲዘመር ምስክር ይሆንባቸዋል። በመሐላ ቃል ወደገባሁላቸው ምድር ከማስገባቴ በፊት አሁን እንኳ ምን ዐይነት ዝንባሌ እንዳላቸው ዐውቃለሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ዛሬ ወደ ማል​ሁ​ላ​ቸው ምድር ገና ሳላ​ገ​ባ​ቸው ክፋ​ታ​ቸ​ውን አው​ቃ​ለ​ሁና፥ ከአ​ፋ​ቸ​ውና ከል​ጆ​ቻ​ቸ​ውም አፍ አት​ረ​ሳ​ምና ብዙ ክፉ ነገ​ርና ጭን​ቀት በደ​ረ​ሰ​ባ​ቸው ጊዜ ይህች መዝ​ሙር ምስ​ክር ሆና በፊ​ታ​ቸው ትቆ​ማ​ለች።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ዛሬ ወደ ማልሁላቸው ምድር ገና ሳላገባቸው የሚያስቡትን አሳብ አውቃለሁና፥ ከልጆቻቸውም አፍ አትረሳምና ብዙ ክፉ ነገርና ጭንቀት በደረሰባቸው ጊዜ ይህች መዝሙር ምስክር ሆና በፊታቸው ትመሰክራለች።

参见章节 复制




ዘዳግም 31:21
16 交叉引用  

እግዚአብሔር አምላክ የሰው ዐመፅ በምድር ላይ የበዛና የልቡም ሐሳብ ዘወትር ወደ ክፋት ብቻ ያዘነበለ መሆኑን ተመለከተ።


እግዚአብሔርም ደስ የሚያሠኘውን መዐዛ አሸተተ፤ በልቡም እንዲህ አለ፤ “ምንም እንኳ ሰው ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ሐሳቡ ወደ ክፋት ያዘነበለ ቢሆንም በርሱ ምክንያት ሁለተኛ ምድርን አልረግማትም፤ አሁን እንዳደረግሁት ሕያዋን ፍጥረታትን ዳግመኛ አላጠፋም።


“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፤ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ስለሚመረምርና ሐሳብን ሁሉ ስለሚያውቅ፣ የአባትህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በበጎ ፈቃድ አገልግለው። ከፈለግኸው ታገኘዋለህ፤ ከተውኸው ግን እርሱም ለዘላለም ይተውሃል።


አንተ መቀመጤንና መነሣቴን ታውቃለህ፤ የልቤንም ሐሳብ ገና ከሩቁ ታስተውላለህ።


የመጨረሻውን ከመጀመሪያው፣ ገና የሚመጣውንም ከጥንቱ ተናግሬአለሁ፤ ‘ምክሬ የጸና ነው፤ ደስ የሚያሠኘኝንም ሁሉ አደርጋለሁ’ እላለሁ።


ስለ ኤፍሬም ሁሉን ዐውቃለሁ፤ እስራኤልም ከእኔ የተሰወረች አይደለችም፤ ኤፍሬም፣ አንተ አሁን አመንዝረሃል፤ እስራኤልም ረክሳለች።


ይኸውም፣ እኔ ጠላት እንድሆንባቸውና ወደ ጠላቶቻቸው ምድር እንድሰድዳቸው ያደረገኝን ኀጢአት ቢናዘዙ፣ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድና ስለ ኀጢአታቸው የሚገባውን ቅጣት ቢቀበሉ፣


እግዚአብሔር በጥንት ውሳኔውና በቀደመው ዕውቀቱ ይህን ሰው አሳልፎ በእጃችሁ ሰጣችሁ፤ እናንተም በክፉ ሰዎች እጅ ሰቅላችሁ ገደላችሁት።


ይህም የሆነው የአንተ ክንድና ፈቃድ ጥንት የወሰኑት እንዲፈጸም ነው።


በርግጥ እንደምትጠፉ እኔ በዛሬው ዕለት እነግራችኋለሁ፤ ዮርዳኖስን ተሻግረህ ትወርሳት ዘንድ በምትገባባት ምድር ብዙ አትኖሩባትም።


ከዚያም ሙሴ ኢያሱን ጠርቶ በእስራኤል ሁሉ ፊት እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው ሊሰጥ ወደ ማለላቸው ምድር ከዚህ ሕዝብ ጋራ ዐብረህ ስለምትገባ፣ ምድሪቱን ርስታቸው አድርገህ ስለምታከፋፍል በርታ፤ ደፋርም ሁን።


ስትጨነቅና ይህ ሁሉ ነገር ሲደርስብህ ያን ጊዜ፣ በኋለኞቹ ዘመናት ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ትመለሳለህ፤ ትታዘዝለታለህም።


跟着我们:

广告


广告