Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 29:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 የሚቀጥለው ትውልድ ከእናንተ በኋላ የሚተኩት ልጆቻችሁና ከሩቅ አገር የሚመጡ እንግዶች በምድሪቱ የደረሰውን ታላቅ መቅሠፍትና እግዚአብሔር ያመጣባቸውን በሽታዎች ያያሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 “የሚቀጥለው ትውልድ ከእናንተ በኋላ የሚተኩት ልጆቻችሁና ከሩቅ አገር የሚመጡ እንግዶች በምድሪቱ የደረሰውን ታላቅ መቅሠፍትና ጌታ ያመጣባቸውን በሽታዎች ያያሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 “በሚመጡት ትውልዶች፥ ዘሮቻችሁና ከሩቅ አገር የመጡ የውጪ አገር ሰዎች እግዚአብሔር በምድራችሁ ላይ ያመጣውን ጥፋትና በሽታ ያያሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 “ከዚ​ያም በኋላ የሚ​ነሣ ትው​ልድ፥ ከእ​ና​ን​ተም በኋላ የሚ​ሆኑ ልጆ​ቻ​ችሁ ከሩቅ ሀገ​ርም የሚ​መጣ እን​ግዳ፥ የዚ​ችን ሀገር መቅ​ሠ​ፍት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በላ​ይዋ የላ​ከ​ውን ሥቃ​ይ​ዋን፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ከዚያም በኋላ የሚነሣ ትውልድ ከእናንተም በኋላ የሚሆኑ ልጆቻችሁ ከሩቅ አገርም የሚመጣ እንግዳ፥ የዚህን አገር መቅሠፍት፥ እግዚአብሔርም በእርስዋ ያደረገውን ሥቃይዋን፥

参见章节 复制




ዘዳግም 29:22
9 交叉引用  

ከዚያም እግዚአብሔር በሰዶምና በገሞራ ላይ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚያቃጥል ዲንና እሳት አዘነበባቸው።


ይህችን ከተማ ድምጥማጧን አጠፋለሁ፤ የድንጋጤና መሣለቂያም ምልክት አደርጋታለሁ፤ በዚያም የሚያልፉ ሁሉ ከቍስሎቿም የተነሣ ወይ ጉድ! ይላሉ፣ ያሾፋሉም።


ያ ሰው እግዚአብሔር ሳይራራ፣ እንደ ገለበጣቸው ከተሞች ይሁን፤ በማለዳ ዋይታን፣ በቀትርም የጦርነትን ውካታ ይስማ፤


“ኤዶም የድንጋጤ ምልክት ትሆናለች፤ ከቍስሎቿም ሁሉ የተነሣ፣ በዚያም የሚያልፉ ሁሉ ወይ ጉድ! ይላሉ።


በዙሪያቸው ካሉት ከተሞች ጋራ፣ ሰዶምና ገሞራ እንደ ተገለበጡ፣” ይላል እግዚአብሔር፤ “እንዲሁ ማንም በዚያ አይኖርም፤ አንድም ሰው አይቀመጥባትም።


ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ባድማ ትሆናለች እንጂ፣ የሚኖርባት አይገኝም፤ በቍስሎቿም ሁሉ ምክንያት፣ በባቢሎን የሚያልፍ ሁሉ ይገረማል፤ ያፌዝባታልም።


“ኤፍሬም ሆይ፤ እንዴት እጥልሃለሁ? እስራኤል ሆይ፤ እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴት እንደ አዳማ አደርግሃለሁ? እንዴትስ እንደ ስቦይ እፈጽምብሃለሁ? ልቤ በውስጤ ተናወጠ፤ ምሕረቴም ሁሉ ተነሣሥቷል።


ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ሞዓብ እንደ ሰዶም፣ አሞናውያን እንደ ገሞራ፣ ዐረም እንደ ዋጠው ቦታና እንደ ጨው ጕድጓድ ለዘላለም ጠፍ ይሆናሉ። ከሕዝቤ የቀሩት ይዘርፏቸዋል፤ ከወገኔ የተረፉትም ምድራቸውን ይወርሳሉ።”


ነገር ግን እሾኽና አሜከላ የምታበቅል መሬት ዋጋ ቢስ ትሆናለች፤ መረገሚያዋም ተቃርቧል፤ መጨረሻዋም በእሳት መቃጠል ነው።


跟着我们:

广告


广告