Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 28:65 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

65 በእነዚያ ሕዝቦች መካከል ዕረፍት አታገኝም፤ ለእግርህም ጫማ ማረፊያ ቦታ አይኖርም። እዚያም እግዚአብሔር የሚጨነቅ አእምሮ፣ በናፍቆት የሚደክም ዐይንና ተስፋ የሚቈርጥ ልብ ይሰጥሃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

65 በእነዚያ ሕዝቦች መካከል ዕረፍት አታገኝም፤ ለእግርህም ጫማ ማረፊያ ቦታ አይኖርም። በዚያም ጌታ የሚርድ ልብ፥ ፈዛዛ ዐይኖች፥ ደካማም ነፍስ ይሰጥሃል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

65 በእነዚያ ሕዝቦች መካከል ዕረፍትና ለእግርህ ማሳረፊያ ቦታ አይኖርህም፤ እግዚአብሔርም የባባ ልብ፥ በናፍቆት የፈዘዘ ዐይን፥ ተስፋ የቈረጠ ስሜት ይሰጥሃል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

65 በእ​ነ​ዚ​ያም አሕ​ዛብ መካ​ከል ዕረ​ፍት አታ​ገ​ኝም፤ ለእ​ግ​ር​ህም ጫማ ማረ​ፊያ አይ​ሆ​ንም፤ በዚ​ያም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተን​ቀ​ጥ​ቃጭ ልብ ፥ ፈዛዛ ዐይን፥ ደካ​ማም ነፍስ ያመ​ጣ​ብ​ሃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

65 በእነዚያም አሕዛብ መካከል ዕረፍት አታገኝም፥ ለእግርህም ጫማ ማረፊያ አይሆንም፤ በዚያም እግዚአብሔር ተንቀጥቃጭ ልብ፥ ፈዛዛ ዓይን፥ ደካማም ነፍስ ያመጣብሃል።

参见章节 复制




ዘዳግም 28:65
21 交叉引用  

ነገር ግን ውሃው የምድርን ገጽ ገና እንደ ሸፈነ ስለ ነበር፣ ተመልሳ ኖኅ ወዳለበት መርከብ መጣች፤ እርሱም እጁን ዘርግቶ ተቀበላት፤ ወደ መርከቢቱም አስገባት።


የክፉዎች ዐይን ግን ትጨልማለች፤ ማምለጫም አያገኙም፤ ተስፋቸውም ሞት ብቻ ነው።”


ከእግዚአብሔር እጅ፣ የቍጣውን ጽዋ የጠጣሽ፣ ዝቃጩ እንኳ ሳይቀር፣ ሰዎችን የሚያንገደግደውን ዋንጫ የጨለጥሽ፣ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ተነሺ!


አምላኬ፣ “ለክፉዎች ሰላም የላቸውም” ይላል።


ባሮቼ፣ ከልብ በመነጨ ደስታ ይዘምራሉ፤ እናንተ ግን፣ ልባችሁ በማዘኑ ትጮኻላችሁ፤ መንፈሳችሁ በመሰበሩም ወዮ ትላላችሁ።


በመከራና በመረገጥ ብዛት ይሁዳ ተማርካ ሄደች፤ በሕዝቦችም መካከል ተቀመጠች፤ የምታርፍበትንም ስፍራ ዐጣች፤ በጭንቀቷ መካከል ሳለች፣ አሳዳጆቿ ሁሉ አገኟት።


በልባቸው ላይ መጋረጃን ዘርጋ፤ ርግማንህም በላያቸው ይሁን!


ከዚህ የተነሣ ልባችን ደከመ፤ ከእነዚህ የተነሣም ዐይናችን ፈዘዘ፤


እኔም ይህን አደርግባችኋለሁ፤ ድንገተኛ ድንጋጤ፣ የሚቀሥፍ በሽታ፣ ዐይናችሁን የሚያጠፋና ሰውነታችሁን የሚያመነምን ትኵሳት አመጣባችኋለሁ፤ እህል የምትዘሩት በከንቱ ነው፤ ጠላቶቻችሁ ይበሉታልና።


“ ‘ከእናንተ በሕይወት የተረፉትን፣ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ ድንጋጤ እሰድድባቸዋለሁ፤ ነፋስ የሚያንቀሳቅሰው የቅጠል ድምፅ ያስበረግጋቸዋል፤ የሚያሳድዳቸውም ሳይኖር ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሮጣሉ፤ ይወድቃሉም።


በጠላቶቻቸው ተነድተው ለምርኮ ቢወሰዱም፣ በዚያ እንዲገድላቸው ሰይፍን አዝዛለሁ። “ለመልካም ሳይሆን ለክፉ፣ ዐይኔን በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ።”


እኔ ሰማሁ፤ ልቤም ደነገጠብኝ፤ ከንፈሬ ከድምፁ የተነሣ ተንቀጠቀጠ፤ ፍርሀት እስከ ዐጥንቴ ዘልቆ ገባ፤ እግሬም ተብረከረከ፤ ሆኖም በሚወርረን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፣ የጥፋትን ቀን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ።


ይህ ሁሉ ግን የምጡ መጀመሪያ ነው።


የሰማያት ኀይላት ስለሚናወጡ፣ ሰዎች በፍርሀትና በዓለም ላይ ምን ይመጣ ይሆን እያሉ በመጠባበቅ ይዝላሉ።


ዐይኖቻቸው እንዳያዩ ይጨልሙ፤ ወገባቸውም ለዘላለም ይጕበጥ።”


ቀንም ሆነ ሌሊት በፍርሀት እንደ ተዋጥህ፣ ሕይወትህ ዋስትና ሳታገኝ፣ ዘወትር በሥጋት ትኖራለህ።


跟着我们:

广告


广告