Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 28:51 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

51 እስክትጠፋም ድረስ የእንስሳትህን ግልገልና የምድርህን ሰብል ይበላል፤ እስኪያጠፋህም ድረስ እህል፣ አዲስ የወይን ጠጅ ሆነ ዘይት፣ የመንጋህን ጥጃ ሆነ የበግና የፍየል መንጋህን ግልገል አያስቀርልህም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

51 እስክትጠፋም ድረስ የከብትህን ፍሬና የምድርህን ፍሬ ይበላል፤ እስኪያጠፋህም ድረስ የእህል፥ የወይን ወይም የዘይት፥ የከብትህን ጥጃ ወይም የበግና ፍየል መንጋህን አይተውልህም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

51 እነርሱ ከብትህንና ሰብልህን ሁሉ ጠራርገው ስለሚበሉት እስክትሞት ድረስ በራብ ትቸገራለህ። እነርሱ አንተ እስክትጠፋ ድረስ ከእህልህ አንዲት ፍሬ፥ ከከብትህ ጥጃ፥ ከበጎችህ መንጋ ጠቦት ከወይንህና ከወይራ ዛፍህ ቅንጣት ፍሬ እንኳ አያስተርፉልህም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

51 እስ​ክ​ት​ጠ​ፋም ድረስ የከ​ብ​ት​ህን ፍሬ፥ የም​ድ​ር​ህ​ንም ፍሬ ይበ​ላል፤ እስ​ኪ​ያ​ጠ​ፋ​ህም ድረስ እህ​ል​ህን፥ ወይ​ን​ህ​ንም፥ ዘይ​ት​ህ​ንም፥ የላ​ም​ህ​ንና የበ​ግ​ህ​ንም መንጋ አይ​ተ​ው​ል​ህም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

51 እስክትጠፋ ድረስ የከብትህን ፍሬ የምድርህንም ፍሬ ይበላሉ፤ እስኪያጠፉህም ድረስ እህልን የወይንም ጠጅ ዘይትንም የላምህንና የበግህን ርቢ አይተዉልህም።

参见章节 复制




ዘዳግም 28:51
13 交叉引用  

በክብር ዘቡ አዛዥ የተመራው መላው የባቢሎን ሰራዊትም በኢየሩሳሌም ዙሪያ የነበረውን ቅጥር አፈረሰው።


አገራችሁ ባድማ፣ ከተሞቻችሁ በእሳት የተቃጠሉ ይሆናሉ፤ ዐይናችሁ እያየ፣ መሬታችሁ በባዕድ ይነጠቃል፤ ጠፍም ይሆናል።


እግዚአብሔር በቀኝ እጁ፣ በኀያል ክንዱም እንዲህ ሲል ምሏል፤ “ከእንግዲህ እህልሽን፣ ለጠላቶችሽ መብል እንዲሆን አልሰጥም፤ ከእንግዲህ የደከምሽበትን፣ አዲስ የወይን ጠጅ ባዕዳን አይጠጡትም።


በመላ አገርህ፣ ስላለው ኀጢአትህ ሁሉ፣ ሀብትና ንብረትህን፣ ያለ ዋጋ አሳልፌ ለምርኮ እሰጣለሁ።


በአገርህ ሁሉ ከተፈጸመው ኀጢአት የተነሣ፣ በምድሪቱ ያለህ ተራራዬ፣ ሀብትህንና ንብረትህን ሁሉ፣ መስገጃ ኰረብቶችህንም ጭምር፣ ለብዝበዛ አደርገዋለሁ።


በራብ ከሚሞቱት ይልቅ፣ በሰይፍ የተገደሉት ይሻላሉ፤ ምግብ በሜዳ ላይ ካለማግኘታቸው የተነሣ፣ በራብ ደርቀው ያልቃሉ።


ለምድሪቱ ሕዝብ እንዲህ በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር በኢየሩሳሌምና በእስራኤል ምድር ስለሚኖሩት እንዲህ ይላል፤ በዚያ ከሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ዐመፅ የተነሣ ምድራቸው ስለምትራቈት፣ ምግባቸውን በጭንቀት ይመገባሉ፤ ውሃቸውንም በፍርሀት ይጠጣሉ።


ለምሥራቅ ሕዝብ ትገዙ ዘንድ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ እነርሱም በመካከላችሁ ይሰፍራሉ፤ ድንኳኖቻቸውንም በዚያ ይተክላሉ፤ ፍሬያችሁን ይበላሉ፤ ወተታችሁንም ይጠጣሉ።


የእንጀራችሁ እህል እንዲቋረጥ በማደርግበት ጊዜ፣ ዐሥር ሴቶች በአንድ ምጣድ ላይ እንጀራ ይጋግራሉ፤ እንጀራውንም በሚዛን መዝነው እናንተም ትበላላችሁ፤ ግን አትጠግቡም።


የምድርህንና የድካምህን ፍሬ ሁሉ የማታውቀው ሕዝብ ይበላዋል፤ ዕድሜ ልክህን በጭካኔና በጭቈና ከመኖር በቀር የሚተርፍህ ነገር አይኖርም።


ሽማግሌ የማያከብር፣ ለብላቴና የማይራራ፣ ሲያዩት የሚያስፈራ ሕዝብ ነው።


የምትታመንባቸውን ታላላቅ የተመሸጉ ቅጥሮች እስኪወድቁ ድረስ በመላው አገርህ ያሉትን ከተሞችህን ሁሉ ይከብባል፤ አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ያሉትን ከተሞች በሙሉ ይወርራቸዋል።


跟着我们:

广告


广告