ዘዳግም 28:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም30 ሚስት ለማግባት ልጃገረድ ታጫለህ፤ ሌላው ግን ወስዶ ይደፍራታል። ቤት ትሠራለህ፣ ግን አትኖርበትም። ወይን ትተክላለህ፤ ፍሬውን ግን አትበላም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)30 “ሚስት ለማግባት ታጫለህ፤ ሌላም ሰው ከእርሷ ጋር ይተኛል። ቤት ትሠራለህ፥ ግን አትኖርበትም። ወይን ትተክላለህ፤ ፍሬውን ግን አትበላም። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም30 “ልጃገረድ ለማግባት ታጫለህ፤ ነገር ግን ሌላ ሰው ይደፍራታል፤ ቤት ትሠራለህ፤ ነገር ግን አትኖርበትም፤ ወይን ትተክላለህ፤ ነገር ግን በፍሬው አትጠቀምበትም። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)30 ሚስት ታገባለህ፤ ሌላም ሰው ይነጥቅሃል፤ ቤት ትሠራለህ፤ በእርሱም አትቀመጥበትም፤ ወይን ትተክላለህ፤ ከእርሱም አትለቅምም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)30 ሚስት ታጫለህ፥ ሌላም ሰው ከእርስዋ ጋር ይተኛል፤ ቤት ትሠራለህ፥ አትቀመጥበትም፤ ወይን ትተክላለህ፥ ከእርሱም አትበላም። 参见章节 |