ዘዳግም 22:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም17 ስሟንም በማጥፋት፣ ‘ልጅህን ከነድንግልናዋ አላገኘኋትም’ ብሎኛል፤ ነገር ግን የልጄ ድንግልና ማረጋገጫ ይኸውላችሁ፤” ከዚያም ወላጆቿ የደሙን ሸማ በከተማዪቱ አለቆች ፊት ይዘርጉት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 እነሆም፦ ‘በልጅህ ድንግልና አላገኘሁባትም’ ብሎ የነውር ነገር አወራባት፥ የልጄም ምልክት ይኸው ይላቸዋል። በከተማም ሽማግሌዎች ፊት ልብሱን ይዘረጋሉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 የልጅህን ድንግልና የሚያመለክት ማስረጃ አላገኘሁም ብሎ የልጄን ስም አጐደፈ፤ ለልጄ የድንግልናዋ ማረጋገጫ ምልክት ይኸውና!’ በማለት በመሪዎቹ ፊት የማስረጃውን ሻሽ ይዘርጋ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 እነሆም፦ በልጅህ ድንግልና አላገኘሁባትም ብሎ የነውር ነገር አወራባት፤ የልጄም የድንግልናዋ ልብስ ይኸው ይላቸዋል። በከተማም ሽማግሌዎች ፊት ልብሱን ይዘረጋሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 እነሆም፦ በልጅህ ድንግልና አላገኘሁባትም ብሎ የነውር ነገር አወራባት፤ የልጄም ምልክት ይኸው ይላቸዋል። በከተማም ሽማግሌዎች ፊት ልብሱን ይዘረጋሉ። 参见章节 |