ዘዳግም 14:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ነገር ግን ከሚያመሰኩት ወይም ሰኰናቸው ከተሰነጠቀ እንስሳት መካከል ግመልን፣ ጥንቸልንና ሽኮኮን አትብሉ፤ እነርሱ ቢያመሰኩ እንኳ፣ ሰኰናቸው የተሰነጠቀ ባለመሆኑ፣ በሥርዐቱ መሠረት በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ናቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ነገር ግን ከሚያመሰኩት ወይም ሰኰናቸው ከተሰነጠቀ እንስሳት መካከል ግመልን፥ ጥንቸልንና ሽኮኮን አትብሉ፤ ምክንያቱም እነርሱ ቢያመሰኩሁም፥ ሰኰናቸው አልተሰነጠቀምና እነዚህ ለእናንተ ርኩሶች ናቸው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ነገር ግን ሰኮናቸው ያልተከፈለውንና የማያመሰኩትን እንስሶች አትብሉ፤ በዚህም ዐይነት ግመል፥ ጥንቸልና ሽኮኮ የመሳሰሉትን አትብሉ፤ እንደነዚህ ያሉት እንስሶች የሚያመሰኩ ቢሆኑም ሰኮናቸው ያልተከፈለ በመሆኑ የረከሱ ሆነው ይቈጠራሉ፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ነገር ግን ከሚያመሰኩ ወይም ሰኰናቸው ከተሰነጠቀ እነዚህን አትበሉም፤ ግመልን፥ ሽኮኮን፥ ጥንቸልን አትበሉም፤ ያመሰኳሉና፥ ነገር ግን ሰኰናቸው አልተሰነጠቀምና እነዚህ ለእናንተ ርኩሳን ናቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ነገር ግን ከሚያመሰኩ ወይም ሰኮናቸው ከተሰነጠቀ እነዚህን አትበሉም፤ ግመልን፥ ጥንቸልን፥ ሽኮኮን አትበሉም። ያመሰኳሉና፥ ነገር ግን ሰኮናቸው አልተሰነጠቀምና እነዚህ ለእናንተ ርኩሶች ናቸው። 参见章节 |