ዘዳግም 12:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም20 አምላክህ እግዚአብሔር በሰጠህ ተስፋ መሠረት ግዛትህን ሲያሰፋልህ፣ ሥጋ አምሮህ፣ “ሥጋ መብላት እፈልጋለሁ” በምትልበት ጊዜ፣ ያሠኘህን ያህል ሥጋ መብላት ትችላለህ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 “አምላክህ ጌታ በሰጠህ ተስፋ መሠረት ግዛትህን ሲያሰፋልህ፥ ሥጋ አምሮህ፥ ‘ሥጋ መብላት እፈልጋለሁ’ በምትልበት ጊዜ፥ ያሰኘህን ያህል ሥጋ መብላት ትችላለህ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 “በሰጠህ ተስፋ መሠረት እግዚአብሔር ግዛትህን በሚያሰፋበት ጊዜ፥ በሚያሰኝህ ጊዜ ሁሉ ሥጋ መመገብ ትችላለህ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 “አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ነገረህ ድንበርህን ባሰፋልህ ጊዜ፥ ሰውነትህም ሥጋ መብላት ስለ ወደደች፦ ሥጋ ልብላ ስትል፥ ሰውነትህ ከወደደችው ሁሉ ብላ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ነገረህ አገርህን ባሰፋ ጊዜ፥ ሰውነትህም ሥጋ መብላት ስለ ወደደች፦ ሥጋ ልብላ ስትል፥ እንደ ሰውነትህ ፈቃድ ሥጋን ብላ። 参见章节 |