Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 11:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 በእግራችሁ የምትረግጡት ስፍራ ሁሉ የእናንተ ይሆናል፤ ግዛታችሁም ከምድረ በዳው እስከ ሊባኖስ፣ ከኤፍራጥስ ወንዝ አንሥቶ በስተምዕራብ እስካለው ባሕር ይደርሳል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 በእግራችሁ የምትረግጡት ስፍራ ሁሉ የእናንተ ይሆናል፤ ግዛታችሁም ከምድረ በዳው እስከ ሊባኖስ፥ ከኤፍራጥስ ወንዝ አንሥቶ በስተ ምዕራብ እስካለው ባሕር ይደርሳል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ስታልፉ በእግራችሁ የምትረግጡት መሬት ሁሉ የእናንተ ይሆናል፤ ግዛታችሁም በደቡብ በኩል ካለው በረሓ ተነሥቶ በሰሜን በኩል እስካሉት እስከ ሊባኖስ ተራራዎች፥ እንዲሁም በምሥራቅ በኩል ከሚገኘው ከኤፍራጥስ ወንዝ ተነሥቶ በምዕራብ በኩል እስከሚገኘው እስከ ታላቁ ሜዲቴራኒያን ባሕር ድረስ ይሰፋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 የእ​ግ​ራ​ችሁ ጫማ የም​ት​ረ​ግ​ጣት ስፍራ ሁሉ ለእ​ና​ንተ ትሆ​ና​ለች፤ ከም​ድረ በዳም፥ ከአ​ን​ጢ​ሊ​ባ​ኖ​ስም፥ ከታ​ላ​ቁም ከኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ባሕር ድረስ ዳር​ቻ​ችሁ ይሆ​ናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 የእግራችሁ ጫማ የምትረግጣት ስፍራ ሁሉ ለእናንተ ትሆናለች፤ ከምድረ በዳም ከሊባኖስም ከታላቁም ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ባሕር ድረስ ዳርቻችሁ ይሆናል።

参见章节 复制




ዘዳግም 11:24
13 交叉引用  

ሰሎሞንም ከወንዙ አንሥቶ እስከ ፍልስጥኤማውያን ምድር፣ ከዚያም እስከ ግብጽ ዳርቻ ያሉትን መንግሥታት ሁሉ ገዛ፤ እነዚህም አገሮች ግብር አመጡለት፤ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ተገዙለት።


ከወንዙ በስተ ምዕራብ፣ ከቲፍሳ እስከ ጋዛ ያሉትን መንግሥታት ስለ ገዛ፣ በሁሉም አቅጣጫ ሰላም ሆኖለት ነበር።


እርሱም ከኤፍራጥስ ወንዝ እስከ ፍልስጥኤም ምድርና እስከ ግብጽ ዳርቻ ድረስ ባሉት ነገሥታት ሁሉ ላይ ገዛ።


“ድንበርህን ከቀይ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፣ ከምድረ በዳው እስከ ወንዙ ድረስ አደርገዋለሁ፤ በምድሪቱም ላይ የሚኖሩትን ሰዎች አሳልፌ እሰጥሃለሁ፤ አንተም አሳድደህ ከፊትህ ታስወጣቸዋለህ።


“የሰሜንን ሰራዊት ከእናንተ አርቃለሁ፤ ፊቱን ወደ ምሥራቁ ባሕር፣ ጀርባውንም ወደ ምዕራቡ ባሕር በማድረግ፣ ወደ ደረቀውና ወደ ባድማው ምድር እገፋዋለሁ፤ ግማቱ ይወጣል፤ ክርፋቱም ይነሣል።” በርግጥ እርሱ ታላቅ ነገር አድርጓል።


ሰፈር ነቅላችሁ ወደ ኰረብታማው የአሞራውያን አገር ጕዞ ቀጥሉ፤ ከዚያም በዓረባ፣ በተራሮቹ፣ በምዕራብ ኰረብቶች ግርጌ፣ በኔጌብና በባሕሩ ዳርቻ ወዳሉት አጐራባች ሕዝቦች ሁሉ ሂዱ፤ እንዲሁም ወደ ከነዓናውያን ምድርና ወደ ሊባኖስ፣ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ ዝለቁ።


እነሆ፤ ይህችን ምድር ሰጥቻችኋለሁ፤ እንግዲህ እግዚአብሔር ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ፣ ከእነርሱም በኋላ ለዘሮቻቸው ሊሰጥ የማለላቸውን ምድር ገብታችሁ ውረሱ።”


አምላክህ እግዚአብሔር በሰጠህ ተስፋ መሠረት ግዛትህን ሲያሰፋልህ፣ ሥጋ አምሮህ፣ “ሥጋ መብላት እፈልጋለሁ” በምትልበት ጊዜ፣ ያሠኘህን ያህል ሥጋ መብላት ትችላለህ።


ንፍታሌምን ሁሉ፣ የኤፍሬምንና የምናሴን ግዛት፣ እስከ ምዕራብ ባሕር ድረስ ያለውን የይሁዳን ምድር ሁሉ፣


ስለዚህም ሙሴ በዚያች ዕለት፣ ‘አምላኬን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ ተከትለኸዋልና እግርህ የረገጣት ምድር ለዘላለም የአንተና የዘርህ ርስት ትሆናለች’ ብሎ ማለልኝ።


跟着我们:

广告


广告