ዳንኤል 9:25 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም25 “ይህን ዕወቅ፤ አስተውለውም፤ ኢየሩሳሌምን ለማደስና ለመጠገን ዐዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ፣ ገዥው መሲሕ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ፣ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል። ኢየሩሳሌም ከጐዳናዎቿና ከቅጥሮቿ ጋራ ትታደሳለች፤ ይህ የሚሆነው ግን በመከራ ጊዜ ነው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 ይህን ልብ ብለህ አስተውል፤ ኢየሩሳሌም እንድትታደስ ትእዛዝ ከወጣበት ጊዜ አንሥቶ መሲሕ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ ሰባት ሳምንቶች ያልፋሉ፤ እንዲሁም ለሥልሳ ሁለት ሳምንት በችግር ጊዜ ኢየሩሳሌም፥ መንገዶችዋና የመከላከያ ጒድጓድዋ ይገነባሉ። ይሁን እንጂ ይህ ሁሉ የመከራ ዘመን ይሆናል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 ስለዚህ እወቅ አስተውልም፥ ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፥ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች። 参见章节 |