Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዳንኤል 8:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እየወጋውና ሁለቱን ቀንዶቹን እየሰበረ፣ በጭካኔ አውራውን በግ ሲጐዳ አየሁ፤ አውራ በጉም ለመቋቋም ጕልበት አልነበረውም። ፍየሉ በምድር ላይ ጥሎ ረገጠው፤ አውራ በጉንም ከፍየሉ እጅ ለማዳን የሚችል አልነበረም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ወደ በጉም ሲጠጋ አየሁት፤ እርሱም በበጉ ላይ በመቈጣት መቶት ሁለት ቀንዶቹን ሰባበረበት፤ በጉም ለመቋቋም የሚያበቃው ኀይል አላገኘም፤ ስለዚህ ፍየሉ ወደ መሬት ጥሎ ረገጠው፤ ከኀይሉም ሊያድነው የሚችል አልነበረም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ወደ አውራውም በግ ሲቀርብ አየሁት፥ እርሱም ተመረረበት፥ አውራውንም በግ መታ፥ ሁለቱንም ቀንዶች ሰበረ፥ አውራውም በግ ሊቋቋመው ኃይል አልነበረውም፥ እርሱም በምድር ላይ ጥሎ ረገጠው፥ አውራውንም በግ ከእጁ ያድነው ዘንድ የሚችል አልነበረም።

参见章节 复制




ዳንኤል 8:7
8 交叉引用  

“ከዚያም የደቡቡ ንጉሥ በቍጣ ወጥቶ የሰሜኑን ንጉሥ ይወጋል። የሰሜኑ ንጉሥ ታላቅ ሰራዊት ቢያሰባስብም ይሸነፋል።


ሌሎቹም አራዊት ሥልጣናቸው ተገፍፎ ነበር፤ ነገር ግን ለተወሰነ ጊዜና ወቅት በሕይወት እንዲኖሩ ተፈቀደላቸው።


“ከዚህ በኋላ በሌሊት ራእይ አየሁ፤ በፊቴም የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ በጣም ኀይለኛ የሆነ አራተኛ አውሬ ነበር፤ ትልልቅ የብረት ጥርሶች ነበሩት፤ ያደቅቅና ይበላ፣ የቀረውንም ሁሉ በእግሮቹ ይረጋግጥ ነበር። ከርሱ በፊት ከነበሩት አራዊት ሁሉ የተለየ ሲሆን፣ ዐሥር ቀንዶች ነበሩት።


ወደ ሰማይ ሰራዊት እስኪደርስ ድረስ አደገ፤ ከከዋክብት ሰራዊትም የተወሰኑትን ወደ ምድር ጣለ፤ ረጋገጣቸውም።


በወንዙ አጠገብ ቆሞ ወዳየሁት፣ ባለሁለት ቀንዶች አውራ በግ ተንደርድሮ መጣበት፤ በታላቅ ቍጣም መታው፤


ፍየሉም ታላቅ ሆነ፤ ነገር ግን በኀይሉ በበረታ ጊዜ፣ ትልቁ ቀንዱ ተሰበረ፤ በቦታውም ወደ አራቱ የሰማይ ነፋሳት የሚያመለክቱ አራት ታላላቅ ቀንዶች በቀሉ።


የሚያሳድዳቸው ሳይኖር ከሰይፍ እንደሚሸሹ እርስ በርሳቸው ይሰነካከላሉ፤ በጠላቶቻችሁም ፊት መቆም አትችሉም።


የጋይ ሰዎች ወደ ኋላ ዞረው ሲመለከቱ የከተማዪቱ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፤ ወደ ምድረ በዳ ይሸሹ የነበሩት እስራኤላውያን ፊታቸውን ስላዞሩባቸውም፣ በየትኛውም በኩል ማምለጫ መንገድ አልነበራቸውም።


跟着我们:

广告


广告