Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዳንኤል 8:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 “የተሰጠህ የምሽቱና የማለዳው ራእይ እውነት ነው፤ ነገር ግን ከብዙ ዘመን በኋላ የሚሆነውን ስለሚያመለክት ራእዩን ዝጋው።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ስለ ጠዋትና ስለ ማታ መሥዋዕት የተነገረው ራእይ እውነት ነው፤ አንተ ግን ይህ ራእይ የሚፈጸምበት ጊዜ ሩቅ ስለ ሆነ በምሥጢር ያዘው” አለኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 የተነገረውም የማታውና የጥዋቱ ራእይ እውነተኛ ነው፥ ነገር ግን ከብዙ ዘመን በኋላ ስለሚሆን ራእዩን ዝጋ።

参见章节 复制




ዳንኤል 8:26
11 交叉引用  

በጕድጓድ ውስጥ እንዳሉ እስረኞች፣ በአንድ ላይ ይታጐራሉ፤ በእስር ቤት ይዘጋባቸዋል፣ ከብዙ ቀንም በኋላ ለፍርድ ይቀርባሉ።


“የሰው ልጅ ሆይ፤ የእስራኤል ቤት፣ ‘ይህ ሰው የሚያየው ራእይ ገና ለሩቅ ዘመን የሚሆን ነው፤ የሚናገረውም ትንቢት የረዥም ጊዜ ትንቢት ነው’ ይላሉ።


የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት፣ ብልጣሶር ለተባለው ዳንኤል ራእይ ታየው። መልእክቱ እውነት ነው፤ ስለ ታላቅ ጦርነትም የሚገልጽ ነበረ። መልእክቱንም ይገነዘብ ዘንድ በራእይ ማስተዋል ተሰጠው።


ራእዩ ሊፈጸም ገና ብዙ ዘመን ስለሚቀረው፣ ወደ ፊት በሕዝብህ ላይ የሚሆነውን ልገልጽልህ አሁን ወደ አንተ መጥቻለሁ።”


“አሁንም እውነቱን እነግርሃለሁ፤ እነሆ፤ ሦስት ሌሎች ነገሥታት በፋርስ ይነሣሉ፤ አራተኛውም ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ እጅግ ባለጠጋ ይሆናል። በባለጠግነቱም እጅግ በበረታ ጊዜ፣ ሌላውን ሁሉ አሳድሞ በግሪክ መንግሥት ላይ ያስነሣል።


ዳንኤል ሆይ፤ አንተ ግን፣ እስከ ፍጻሜው ዘመን ድረስ የመጽሐፉን ቃል ዝጋ፤ ዐትመውም። ብዙዎች ወዲያ ወዲህ ይራወጣሉ፤ ዕውቀትም ይበዛል።”


እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ዳንኤል ሆይ፤ ቃሉ እስከ ፍጻሜው ዘመን ድረስ የተዘጋና የታተመ ስለ ሆነ ሂድ።


ሰባቱ ነጐድጓዶች በተናገሩ ጊዜ፣ ለመጻፍ ተዘጋጀሁ፤ ነገር ግን፣ “ሰባቱ ነጐድጓዶች የተናገሩትን በማኅተም ዝጋው እንጂ አትጻፍ” የሚል ድምፅ ከሰማይ ሰማሁ።


እንዲህም አለኝ፤ “ጊዜው ስለ ደረሰ፣ የዚህን መጽሐፍ የትንቢት ቃል በማኅተም አትዝጋው፤


跟着我们:

广告


广告