Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አሞጽ 5:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 በየወይኑ ዕርሻ ሁሉ ወየው ተብሎ ይለቀሳል፤ እኔ በመካከላችሁ ዐልፋለሁና፤” ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በመካከልህ አልፋለሁና በወይኑ ቦታ ሁሉ ልቅሶ ይሆናል፥” ይላል ጌታ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 በወይን ተክል ቦታዎች ሁሉ ለቅሶ ይሆናል፤ ይህም ሁሉ የሚሆነው እኔ በመካከላችሁ ስለማልፍ ነው፤” ይህንንም የተናገረ እግዚአብሔር ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በመ​ካ​ከ​ልህ አል​ፋ​ለ​ሁና በጎ​ዳ​ናው ሁሉ ልቅሶ ይሆ​ናል” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በመካከልህ አልፋለሁና በወይኑ ቦታ ሁሉ ልቅሶ ይሆናል፥ ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制




አሞጽ 5:17
11 交叉引用  

ከዚህ በኋላ ሙሴ እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ ‘እኩለ ሌሊት ሲሆን በመላው የግብጽ ምድር ላይ ዐልፋለሁ።


“እኔም በዚያች ሌሊት በግብጽ ምድር ላይ ዐልፋለሁ፤ ከሰውም ከእንስሳም የተወለደውን የበኵር ልጅ ሁሉ እገድላለሁ፤ የግብጽን አማልክት ሁሉ እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


እግዚአብሔር ግብጻውያንን ለመቅሠፍ በምድሪቱ ላይ በሚያልፍበት ጊዜ በጕበኑና በመቃኑ ላይ ያለውን ደም ሲያይ ያን ደጃፍ ዐልፎ ይሄዳል፤ ቀሣፊውም ወደ ቤታችሁ ገብቶ እንዳይገድላችሁ ይከለክለዋል።


ደስታና ሐሤትም ከአትክልቱ ቦታ ተወግዷል፤ በወይን ተክልም ቦታ ዝማሬ የለም፤ እልልታም ቀርቷል። በወይን መጭመቂያ ቦታ የሚረግጥ የለም፤ የረጋጮችን ሆታ አጥፍቻለሁና።


ከሞዓብ የአትክልት ቦታና ዕርሻ፣ ሐሤትና ደስታ ርቋል፤ የወይን ጠጅ ከመጭመቂያው እንዳይወርድ አድርቄዋለሁ፤ በእልልታ የሚጨምቀውም አይገኝም፤ በዚያ ድምፅ ቢሰማም፣ የእልልታ ድምፅ አይደለም።


“ከዚያም እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር፣ በቅዱሱ ተራራዬ በጽዮን እንደምኖር ታውቃላችሁ፤ ኢየሩሳሌም የተቀደሰች ትሆናለች፤ ከእንግዲህም ወዲያ ባዕዳን አይወርሯትም።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ምንም ኀይለኞችና ብዙዎች ቢሆኑም፣ ይቈረጣሉ፤ ይጠፋሉም። ይሁዳ ሆይ፤ ከዚህ በፊት ባስጨንቅህም፣ ከእንግዲህ አላስጨንቅህም።


እነሆ፤ የምሥራች የሚያመጣው፣ ሰላምን የሚያውጀው ሰው እግር፣ በተራሮች ላይ ነው፤ ይሁዳ ሆይ፤ በዓላትህን አክብር፤ ስእለትህንም ፈጽም፤ ከእንግዲህ ምናምንቴ ሰዎች አይወርሩህም፤ እነርሱም ፈጽመው ይጠፋሉ።


እኔ ግን ቤቴን ከዘራፊ ኀይሎች እጠብቃለሁ፤ ጨቋኝ ከእንግዲህ ሕዝቤን አይወርስም፤ አሁን ነቅቼ እጠብቃለሁና።


跟着我们:

广告


广告