Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 8:31 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ጃንደረባውም፣ “የሚያስረዳኝ ሰው ሳይኖር እንዴት አድርጌ አስተውላለሁ” አለው፤ እርሱም ወደ ሠረገላው ወጥቶ ዐብሮት እንዲቀመጥ ፊልጶስን ለመነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 እርሱም “የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዴት ይቻለኛል?” አለው። ወጥቶም ከእርሱ ጋር ይቀመጥ ዘንድ ፊልጶስን ለመነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ኢትዮጵያዊውም “የሚያስረዳኝ ሰው ሳይኖር እንዴት ሊገባኝ ይችላል?” አለና ፊልጶስን “ወደ ሠረገላው ውጣና ከእኔ ጋር ተቀመጥ” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ጃን​ደ​ረ​ባ​ውም፥ “ያስ​ተ​ማ​ረኝ ሳይ​ኖር በምን አው​ቀ​ዋ​ለሁ?” አለው፤ ወደ ሰረ​ገ​ላ​ውም ወጥቶ አብ​ሮት ይቀ​መጥ ዘንድ ፊል​ጶ​ስን ለመ​ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 እርሱም፦ “የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዴት ይቻለኛል?” አለው። ወጥቶም ከእርሱ ጋር ይቀመጥ ዘንድ ፊልጶስን ለመነው።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 8:31
20 交叉引用  

ኤልሳዕ ግን እንዲህ አለው፤ “ያ ሰው ሊገናኝህ ከሠረገላው ሲወርድ፣ መንፈሴ ከአንተ ጋራ አልሄደምን? እንዲያው ለመሆኑ ጊዜው ገንዘብና ልብስ፣ የወይራ ዘይት ተክልና የወይን ተክል ቦታ፣ የበግና የከብት መንጋ፣ ወንድና ሴት አገልጋይ የሚቀበሉበት ነውን?


ስለዚህ ንዕማን በፈረሶቹና በሠረገሎቹ ሆኖ በኤልሳዕ ቤት ደጃፍ ሲደርስ ቆመ።


ደነዝና አላዋቂ ሆንሁ፤ በፊትህም እንደ እንስሳ ሆንሁ።


በዚያ አውራ ጐዳና ይሆናል፤ የተቀደሰ መንገድ ተብሎ ይጠራል። የረከሱ አይሄዱበትም፤ በመንገዱ ላይ ላሉት ብቻ ይሆናል፤ ቂሎችም አይሄዱም።


እውነት እላችኋለሁ፤ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀበል ሁሉ ከቶ አይገባባትም።”


ፊልጶስም ፈጥኖ ወደ ሠረገላው ሄደ፤ ጃንደረባውም የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብብ ሰምቶ፣ “ለመሆኑ፣ የምታነብበውን ታስተውለዋለህን?” አለው።


ጃንደረባው ያነብብ የነበረው የመጽሐፍ ክፍል ይህ ነበር፤ “እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፤ በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ፣ አፉን አልከፈተም።


ታዲያ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል? ስለ እርሱስ ሳይሰሙ እንዴት ያምኑበታል? ሰባኪ ሳይኖር እንዴት መስማት ይችላሉ?


ማንም ራሱን አያታልል፤ ከእናንተ ማንም በዚህ ዓለም ጥበበኛ የሆነ ቢመስለው፣ ጥበበኛ ይሆን ዘንድ ራሱን እንደ ሞኝ ይቍጠር።


ዐውቃለሁ የሚል ሰው፣ ማወቅ የሚገባውን ያህል ገና አላወቀም።


ባለጠጋውም ዝቅ በማለቱ ይመካ፤ እንደ ሣር አበባ ይረግፋልና።


ስለዚህ ርኩሰትንና ተንሰራፍቶ የሚገኘውን ክፋትን አስወግዳችሁ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን፣ በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በትሕትና ተቀበሉ።


跟着我们:

广告


广告