Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 27:33 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ልክ ሊነጋጋ ሲል፣ ጳውሎስ ሁሉም ምግብ እንዲበሉ እንዲህ ሲል ለመናቸው፤ “ዐሥራ አራት ቀን ሙሉ ልባችሁ ተንጠልጥሎ ምንም ሳትቀምሱ ጦማችሁን ሰነበታችሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ቀንም ሲነጋ ጳውሎስ ምግብ ይበሉ ዘንድ ሁሉን ይለምን ነበር፤ እንዲህም አላቸው “እየጠበቃችሁ ምንም ሳትቀበሉ ጦማችሁን ከሰነበታችሁ ዛሬ ዐሥራ አራተኛ ቀናችሁ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ቀኑ ሊነጋ ሲል ሁሉም ምግብ እንዲመገቡ ጳውሎስ ለመናቸው፤ እንዲህም አላቸው፦ “ምንም እህል ሳትቀምሱ በመጠባበቅ ከሰነበታችሁ ዛሬ ዐሥራ አራተኛ ቀናችሁ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ሊነ​ጋም በጀ​መረ ጊዜ ጳው​ሎስ እህል እን​ዲ​በሉ ሁሉ​ንም ማለ​ዳ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እህል ከተ​ዋ​ችሁ ዛሬ ዐሥራ አራት ቀን ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ቀንም ሲነጋ ጳውሎስ ምግብ ይበሉ ዘንድ ሁሉን ይለምን ነበር፥ እንዲህም አላቸው፦ “እየጠበቃችሁ ምንም ሳትቀበሉ ጦማችሁን ከሰነበታችሁ ዛሬ አሥራ አራተኛ ቀናችሁ ነው።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 27:33
6 交叉引用  

“ሂድና በሱሳ ያሉትን አይሁድ ሁሉ በአንድነት ሰብስብ፤ ስለ እኔም ጹሙልኝ፤ ቀንም ይሁን ሌሊት ለሦስት ቀን አትብሉ፤ አትጠጡም። እኔና ደንገጡሮቼም እናንተ እንደምታደርጉት ሁሉ እንጾማለን፤ ይህ ከተፈጸመ በኋላ ግን ነገሩ ምንም እንኳ ከሕግ ውጭ ቢሆንም፣ ወደ ንጉሡ ዘንድ እሄዳለሁ፤ ከጠፋሁም ልጥፋ።”


ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ራሱ ጠርቶ፣ “ሕዝቡ ከእኔ ጋራ ሦስት ቀን ስለ ሆናቸውና የሚበሉት ስለሌላቸው ለእነዚህ ሰዎች ዐዝንላቸዋለሁ፤ በመንገድ ላይ በራብ ዝለው እንዳይወድቁ ጦማቸውን ልሰድዳቸው አልፈቅድም” አለ።


ሰዎቹ እህል ሳይቀምሱ ብዙ ቀን ከቈዩ በኋላ፣ ጳውሎስ በመካከላቸው ቆሞ እንዲህ አለ፤ “እናንተ ሰዎች ሆይ፤ የነገርኋችሁን ሰምታችሁ ቢሆን ኖሮ፣ ከቀርጤስ ባልተነሣችሁና ይህ ጕዳትና ጥፋት ባልደረሰባችሁ ነበር።


በዚህ ጊዜ ወታደሮቹ ገመዶቹን ቈርጠው ትንሿ ጀልባ ባሕሩ ላይ ተንሳፍፋ እንድትቀር ለቀቋት።


ስለዚህ፣ ለደኅንነታችሁ አሁን እህል እንድትቀምሱ እለምናችኋላሁ፤ ከእናንተ መካከል ከራሱ ጠጕር አንዲት እንኳ የሚነካበት ማንም የለምና።”


ምግብም በልቶ በረታ። ሳውል በደማስቆ ከነበሩት ደቀ መዛሙርት ጋራ አያሌ ቀን ተቀመጠ።


跟着我们:

广告


广告