Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 27:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ክረምቱንም በዚያ ለማሳለፍ ወደቡ አመቺ ስላልነበረ፣ አብዛኛዎቹ ፍንቄ ወደተባለው ወደብ ደርሰው በዚያ ለመክረም ተስፋ በማድረግ ጕዟችንን እንድንቀጥል ውሳኔ አስተላለፉ፤ ወደቡም በቀርጤስ ደቡብ ምዕራብና ሰሜን ምዕራብ ትይዩ የሚገኝ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ያም ወደብ ይከርሙበት ዘንድ የማይመች ስለ ሆነ፥ የሚበዙቱ ቢቻላቸው በሰሜንና በደቡብ ምዕራብ ትይዩ ወዳለው ፍንቄ ወደሚሉት ወደ ቀርጤስ ወደብ ደርሰው ይከርሙ ዘንድ ከዚያ እንዲነሡ መከሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ያ ወደብ ለክረምት ማሳለፊያ ምቹ ስላልነበረ አብዛኞቹ ሰዎች “ጒዞአቸውን ቀጥለው የሚቻል ቢሆን በሰሜን ምዕራብና በደቡብ ምዕራብ በር ወዳለው ፊንቄ ወደሚባለው የቀርጤስ ወደብ ደርሰን ክረምቱን እዚያ እናሳልፍ” ብለው አሳብ አቀረቡ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ያም ወደብ ክረ​ም​ቱን ሊከ​ር​ሙ​በት የማ​ይ​መች ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም ብዙ​ዎች ከዚያ ይወጡ ዘንድ ይቻ​ላ​ቸው እንደ ሆነ በቀኝ በኩል ወደ አለው ፊንቄ ወደ​ሚ​ባ​ለው ወደ ሁለ​ተ​ኛው የቀ​ር​ጤስ ወደብ ይደ​ርሱ ዘንድ ወደዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ያም ወደብ ይከርሙበት ዘንድ የማይመች ስለ ሆነ፥ የሚበዙቱ ቢቻላቸው በሰሜንና በደቡብ ምዕራብ ትይዩ ወዳለው ፍንቄ ወደሚሉት ወደ ቀርጤስ ወደብ ደርሰው ይከርሙ ዘንድ ከዚያ እንዲነሡ መከሩ።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 27:12
8 交叉引用  

ጸጥ በማለቱም ደስ አላቸው፤ ወዳሰቡትም ወደብ አደረሳቸው።


አይሁድና ወደ ይሁዲነት የገባን፣ የቀርጤስና የዐረብ ሰዎች ስንሆን፣ ሰዎቹ የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ በየቋንቋችን ሲናገሩ እንሰማቸዋለን!”


መጠነኛ የደቡብ ነፋስ በነፈሰ ጊዜም እንዳሰቡት የሆነላቸው መስሏቸው መልሕቁን ነቅለው፣ የቀርጤስን ዳርቻ በመያዝ ተጓዙ።


ሰዎቹ እህል ሳይቀምሱ ብዙ ቀን ከቈዩ በኋላ፣ ጳውሎስ በመካከላቸው ቆሞ እንዲህ አለ፤ “እናንተ ሰዎች ሆይ፤ የነገርኋችሁን ሰምታችሁ ቢሆን ኖሮ፣ ከቀርጤስ ባልተነሣችሁና ይህ ጕዳትና ጥፋት ባልደረሰባችሁ ነበር።


ብዙ ቀን በዝግታ እየተጓዝን ቀኒዶስ አካባቢ በጭንቅ ደረስን፤ ነፋሱም ወደ ፊት እንዳንሄድ በከለከለን ጊዜ፣ በሰልሙና አጠገብ አድርገን በቀርጤስ ተተግነን ሄድን፤


ጥግ ጥጉንም ይዘን፣ በላሲያ ከተማ አጠገብ ወዳለው፣ “መልካም ወደብ” ወደ ተባለ ስፍራ በጭንቅ ደረስን።


ከራሳቸው ነቢያት አንዱ ስለ እነርሱ ሲናገር፣ “የቀርጤስ ሰዎች ዘወትር ውሸታሞች፣ ክፉ አውሬዎችና ሰነፍ ሆዳሞች ናቸው” ብሏል።


አንተን በቀርጤስ የተውሁህ ገና ያልተስተካከለውን ነገር እንድታስተካክልና ባዘዝሁህ መሠረት በየከተማው ሽማግሌዎችን እንድትሾም ነው።


跟着我们:

广告


广告