Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 26:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 አግሪጳም ጳውሎስን፣ “ስለ ራስህ እንድትናገር ተፈቅዶልሃል” አለው። በዚህ ጊዜ ጳውሎስ እጁን ዘርግቶ እንዲህ ሲል መከላከያውን አቀረበ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 አግሪጳም ጳውሎስን “ስለ ራስህ ትናገር ዘንድ ተፈቅዶልሃል፤” አለው። በዚያን ጊዜ ጳውሎስ እጁን ዘርግቶ እንዲህ ሲል መለሰ፦

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 አግሪጳ ጳውሎስን “ስለ ራስህ እንድትናገር ተፈቅዶልሃል” አለው፤ ጳውሎስም እጁን ዘረጋና እንዲህ ሲል የመከላከያ መልሱን ሰጠ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አግ​ሪ​ጳም ጳው​ሎ​ስን፥ “ስለ ራስህ ትና​ገር ዘንድ ፈቅ​ደ​ን​ል​ሃል” አለው፤ ከዚ​ህም በኋላ ጳው​ሎስ እጁን አነ​ሣና ይነ​ግ​ራ​ቸው ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 አግሪጳም ጳውሎስን፦ “ስለ ራስህ ትናገር ዘንድ ተፈቅዶልሃል” አለው። በዚያን ጊዜ ጳውሎስ እጁን ዘርግቶ መለሰ እንዲህ ሲል፦

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 26:1
12 交叉引用  

ምስክርነትህን በነገሥታት ፊት እናገራለሁ፤ ይህን በማድረግም ዕፍረት አይሰማኝም።


ነገር ግን በተጣራሁ ጊዜ እንቢ ስላላችሁኝ፣ እጄንም ስዘረጋ ማንም ግድ ስላልነበረው፣


ከማዳመጡ አስቀድሞ የሚመልስ፣ ቂልነትና ዕፍረት ይሆንበታል።


አስቀድሞ ጕዳዩን የሚያሰማ ትክክለኛ ይመስላል፤ ይኸውም ባላንጣው መጥቶ እስከሚመረመር ድረስ ነው።


ስለዚህ ክንዴን በአንቺ ላይ አንሥቼ ድርጎሽን ቀነስሁ፤ ከክፉ መንገድሽም የተነሣ በብልግናሽ ለሚያፍሩ ጠላቶችሽ ለፍልስጥኤማውያን ሴቶች ልጆች አሳልፌ ሰጠሁሽ።


“ሕጋችን፣ አስቀድሞ አንድን ሰው ሳይሰማና ምን እንዳደረገ ሳይረዳ ይፈርድበታልን?”


“ወንድሞችና አባቶች ሆይ፤ አሁን የማቀርብላችሁን የመከላከያ መልሴን ስሙኝ።”


“እኔም፣ ተከሳሽ በከሳሾቹ ፊት ቆሞ ለተከሰሰበት ነገር መልስ ለመስጠት ዕድል ሳያገኝ፣ አሳልፎ መስጠት የሮማውያን ልማድ እንዳልሆነ ነገርኋቸው።


ይኸውም አንድ እስረኛ ወደ በላይ ሲላክ የተከሰሰበትን ምክንያት አለመግለጽ ትክክል ስላልመሰለኝ ነው።”


“ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፤ አይሁድ በእኔ ላይ ላቀረቡት ክስ ሁሉ ዛሬ በፊትህ የመከላከያ መልስ ለማቅረብ በመቻሌ ራሴን እንደ ዕድለኛ እቈጥረዋለሁ፤


ጌታም እንዲህ አለው፤ “ሂድ! ይህ ሰው በአሕዛብና በነገሥታት ፊት እንዲሁም በእስራኤል ሕዝብ ፊት ስሜን እንዲሸከም የተመረጠ ዕቃዬ ነው፤


ስለ እስራኤል ግን፣ “ወደማይታዘዝና ዕሺ ወደማይል ሕዝብ፣ ቀኑን ሙሉ እጆቼን ዘረጋሁ” ይላል።


跟着我们:

广告


广告