Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 19:40 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 አለዚያ ዛሬ ስለ ሆነው ነገር፣ በሁከት አነሣሽነት እንዳንከሰስ ያሠጋናል፤ አጥጋቢ ምክንያት ስለሌለንም፣ ስለ ሁከቱ ብንጠየቅበት መልስ መስጠት አንችልም።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ዛሬ ስለተደረገው ‘ሁከት ነው፤’ ሲሉ እንዳይከሱን ያስፈራልና፤ ስለዚህም ስብሰባ ምላሽ መስጠት አንችልም፤ ምክንያት የለምና።” ይህንም ብሎ ጉባኤውን ፈታው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 አለበለዚያ ዛሬ በተደረገው ነገር ‘ሁከት አስነሥተዋል’ ተብለን እንዳንከሰስ ያስፈራል፤ ‘ይህ ብጥብጥ በምን ምክንያት ተነሣ’ ተብለን ብንጠየቅ የምንሰጠው መልስ የለንም”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 ዛሬም በደል ሳይ​ኖር በአ​መ​ጣ​ች​ሁ​ብን ክር​ክር እኛ እን​ቸ​ገ​ራ​ለ​ንና ስለ​ዚህ ክር​ክር የም​ን​ወ​ቃ​ቀ​ሰው ነገር የለም፥” ይህ​ንም ብሎ ሸን​ጎ​ውን ፈታ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ዛሬ ስለ ተደረገው፦ ሁከት ነው ሲሉ እንዳይከሱን ያስፈራልና፤ ስለዚህም ስብሰባ ምላሽ መስጠት አንችልም፥ ምክንያት የለምና።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 19:40
10 交叉引用  

አዶንያስና የተጠሩት እንግዶች ሁሉ ግብዣውን በማገባደድ ላይ ሳሉ፣ ይህንኑ ሰሙ፤ ኢዮአብም የመለከቱን ድምፅ ሲሰማ፣ “ይህ በከተማዪቱ ውስጥ የሚሰማው ድምፅ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀ።


ነገር ግን፣ “በሕዝቡ መካከል ረብሻ እንዳይነሣ በበዓል ቀን አይሁን” በማለት ተስማሙ።


በእኛ መካከል ስለ ተፈጸሙት ነገሮች ብዙዎች ታሪኩን የተቻላቸውን ያህል ጽፈውት ይገኛል፤


ከዚህ ሌላ ልታቀርቡ የፈለጋችሁት ነገር ካለ በሕጋዊ ጉባኤ ይታያል።


ይህን ከተናገረ በኋላም ጉባኤው እንዲበተን አደረገ።


ሁከቱም እንደ በረደ፣ ጳውሎስ ደቀ መዛሙርትን አስጠርቶ መከራቸው፤ ተሰናብቷቸውም ወደ መቄዶንያ ለመሄድ ተነሣ።


ሊገድሉት ሲፈልጉም የኢየሩሳሌም ከተማ ፍጹም ታወከች፤ ወሬውም ለሮማ ጦር አዛዥ ደረሰው።


አንተ ከዚህ ቀደም ዐመፅ አስነሥተህ፣ አራት ሺሕ ነፍሰ ገዳዮችን ወደ በረሓ ያሸፈትኸው ግብጻዊ አይደለህምን?”


ፊልክስ ግን የጌታን መንገድ በሚገባ ዐውቆ ስለ ነበር፣ “የጦር አዛዡ ሉስያስ ሲመጣ ለጕዳያችሁ ውሳኔ እሰጣለሁ” ብሎ ነገሩን በቀጠሮ አሳደረው።


跟着我们:

广告


广告