Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 16:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ድንገትም የወህኒ ቤቱን መሠረት የሚያናውጥ ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ሆነ፤ ወዲያውም የወህኒ ቤቱ በሮች ተከፈቱ፤ የሁሉም እስራት ተፈታ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ፤ የሁሉም እስራት ተፈታ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 በድንገት የወህኒ ቤቱ መሠረት እስኪናጋ ድረስ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ በሮቹም ሁሉ በአንድ ጊዜ ተከፈቱ፤ የእያንዳንዱም እስረኛ ሰንሰለት ተፈታ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ድን​ገ​ትም ታላቅ ንው​ጽ​ው​ጽታ ሆነ፤ የወ​ህኒ ቤቱ መሠ​ረ​ትም ተና​ወጠ፤ በሮ​ችም ሁሉ ያን​ጊዜ ተከ​ፈቱ፤ የሁ​ሉም እግር ብረ​ቶ​ቻ​ቸው እየ​ወ​ለቁ ወደቁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ የሁሉም እስራት ተፈታ።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 16:26
15 交叉引用  

ከዚያም ሄዶ ሬሳው መንገድ ላይ ተጋድሞ አንበሳውና አህያው በአጠገቡ ቆመው አገኘ፤ አንበሳው ሬሳውን አልበላውም፤ አህያውንም አልሰበረውም።


ይኸውም የእስረኞችን ጩኸት ይሰማ ዘንድ፣ ሞት የተፈረደባቸውንም ያድን ዘንድ ነው።”


ለተበደሉት የሚፈርድ፣ ለተራቡት ምግብን የሚሰጥ እርሱ ነው፤ እግዚአብሔር እስረኞችን ከእስራት ያወጣል፤


እግዚአብሔር ብቸኞችን በቤተ ሰብ መካከል ያኖራል፤ እስረኞችን ነጻ አውጥቶ ያስፈነድቃል፤ ዐመፀኞች ግን ምድረ በዳ ይኖራሉ።


የእስረኞች ሰቈቃ በፊትህ ይድረስ፤ በክንድህም ብርታት፣ ሞት የተፈረደባቸውን አድን።


የዕውሮችን ዐይን ትከፍታለህ፤ ምርኮኞችን ከእስር ቤት፣ በጨለማ የተቀመጡትንም ከወህኒ ታወጣለህ።


የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድኾች ወንጌልን እንድሰብክ፣ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና። ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፣ ለምርኮኞች ነጻነትን፣ ለእስረኞች መፈታትን እንዳውጅ ልኮኛል።


በድንገት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ የጌታም መልአክ ከሰማይ ወርዶ ወደ መቃብሩ በመሄድ ድንጋዩን አንከባልሎ በላዩ ላይ ተቀመጠበት፤


የመጀመሪያውንና ሁለተኛውን ዘብ ዐልፈው ወደ ከተማዪቱ በሚወስደው መንገድ ላይ ወዳለው የብረት መዝጊያ ዘንድ ደረሱ። መዝጊያውም ራሱ ዐውቆ ተከፈተላቸው፤ እነርሱም ወጥተው ሄዱ፤ አንዲት ስላች መንገድ እንዳለፉም ወዲያው መልአኩ ተለየው።


የጌታ መልአክም ድንገት ታየ፤ በክፍሉም ውስጥ ብርሃን በራ፤ መልአኩም የጴጥሮስን ጐን መታ አድርጎ ቀሰቀሰውና፣ “ቶሎ ተነሣ!” አለው፤ በዚህ ጊዜ ሰንሰለቶቹ ከእጆቹ ወደቁ።


ከጸለዩም በኋላ የነበሩበት ስፍራ ተናወጠ፤ ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ፤ የእግዚአብሔርንም ቃል በድፍረት ተናገሩ።


ይሁን እንጂ የጌታ መልአክ በሌሊት የእስር ቤቱን ደጆች ከፍቶ አወጣቸውና፣


በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ የከተማዪቱም አንድ ዐሥረኛ ወደመ፤ በነውጡም ሰባት ሺሕ ሰዎች ሞቱ፤ የተረፉትንም ፍርሀት ያዛቸው፤ ለሰማይም አምላክ ክብር ሰጡ።


ስድስተኛውን ማኅተም ሲፈታ ተመለከትሁ፤ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ፀሓይም እንደ ማቅ ጠቈረች፤ ጨረቃም በሙሉ እንደ ደም ቀላች።


跟着我们:

广告


广告