Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 3:34 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 እጆችህ አልታሰሩም፤ እግሮችህ በእግር ብረት አልገቡም፤ ሰው በክፉ ሰዎች ፊት እንደሚወድቅ አንተም እንደዚሁ ወደቅህ።” ሕዝቡም ሁሉ እንደ ገና አለቀሱለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 “አበኔር እንደ ተራ ሰው ይሙት? እግሮችህ በእግር ብረት አልገቡም፤ ሰው በክፉ ሰዎች ፊት እንደሚወድቅ አንተም እንደዚሁ ወደቅህ።” ሕዝቡም ሁሉ እንደገና አለቀሱለት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 እጆችህ አልታሰሩም፤ እግሮችህ አልታበቱም፤ ታዲያ፥ በዚህ ሁኔታ ሳለ በወንጀለኞች እጅ እንደሚወድቅ ሰው እንዴት ተገደልክ!” ሕዝቡም ሁሉ ስለ እርሱ እንደገና አለቀሱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 እጆ​ችህ አል​ታ​ሰ​ሩም፤ እግ​ሮ​ች​ህም በሰ​ን​ሰ​ለት አል​ተ​ያ​ዙም፤ ማንም እንደ ሰነፍ አል​ወ​ሰ​ደ​ህም፤ በዐ​መፃ ልጆ​ችም ፊት ወደ​ቅህ።” ሕዝ​ቡም ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው አለ​ቀ​ሱ​ለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 እጅህ አልታሰረም፥ እግርህም በሰንሰለት አልተያዘም፥ ሰው በዓመፀኞች ፊት እንደሚወድቅ አንተ እንዲሁ ወደቅህ ብሎ የልቅሶ ቅኔ ተቀኘለት። ሕዝቡም ሁሉ ዋይታ አብዝተው አለቀሱ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 3:34
8 交叉引用  

ለሳኦልና ለልጁ ለዮናታን፣ ለእግዚአብሔር ሰራዊትና ለእስራኤል ቤት ዐዘኑ፤ አለቀሱ፤ እስከ ማታም ድረስ ጾሙ፤ የወደቁት በሰይፍ ነበርና።


ንጉሡም ለአበኔር ይህን የሐዘን እንጕርጕሮ ተቀኘ፤ “አበኔር እንደ ሞኝ ሰው ይሙት?


ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ እህል በሚቀምስበት ሰዓት ወደ ዳዊት መጥተው ምግብ እንዲበላ አጥብቀው ለመኑት። ዳዊት ግን፣ “ፀሓይ ከመጥለቋ በፊት እንጀራ ወይም ሌላ ነገር ብቀምስ፣ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፤ ከዚህም የባሰ ያምጣብኝ” ብሎ ማለ።


ቀኑ ሲመሽ፣ ነፍሰ ገዳይ ይነሣል፤ ችግረኞችንና ድኾችን ይገድላል፤ በሌሊትም እንደ ሌባ ያደባል፤


“ስለ እርሷ የሚያወርዱት ሙሾ ይህ ነው፤ የሕዝቦች ሴት ልጆች ያዜሙታል፤ ስለ ግብጽና ስለ ብዙ ሰራዊቷ ሁሉ ሙሾ ያወርዳሉ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”


ወንበዴዎች ሰውን ለማጥቃት እንደሚያደቡ፣ ካህናትም በቡድን እንዲሁ ያደርጋሉ፤ በሴኬም መንገድ ላይ ሰዎችን ይገድላሉ፤ አሳፋሪም ወንጀል ይፈጽማሉ።


ከዚያም ፍልስጥኤማውያን ያዙት፤ ዐይኖቹን አውጥተው ወደ ጋዛ ይዘውት ወረዱ፤ በናስ ሰንሰለት አስረውም እስር ቤት ውስጥ እህል እንዲፈጭ አደረጉት።


跟着我们:

广告


广告