2 ሳሙኤል 2:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም16 ከዚያም እያንዳንዱ ሰው የባላጋራውን ራስ በመያዝ ሰይፉን በጐኑ እየሻጠበት ተያይዘው ወደቁ። ስለዚህም በገባዖን የሚገኘው ያ ቦታ “የሰይፍ ምድር” ተባለ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ከዚያም እያንዳንዱ ሰው የባለጋራውን ራስ ያዘ፥ ሰይፉንም በጐኑ ሻጠ፥ ተያይዘውም ወደቁ። ስለዚህም በገባዖን የሚገኘው ያ ስፍራ “የስለታም ሰይፍ ምድር” ተባለ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 እያንዳንዱ ሰው የባለጋራውን ራስ ይዞ ሰይፉን በጐኑ ሻጠበት፤ በዚህ ዐይነት ኻያ አራቱም ሰዎች በአንድነት ወድቀው ሞቱ፤ ስለዚህም በገባዖን የሚገኘው ያ ስፍራ “የሰይፍ ምድር” ተብሎ ተጠራ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ሁሉም እያንዳንዱ የወደረኛውን ራስ በእጁ ያዘ፤ ሰይፉንም በወደረኛው ጐን ሻጠ፤ ተያይዘውም ወደቁ። የዚያም ስፍራ ስም “በገባዖን የሸመቁ ሰዎች ድርሻ” ተብሎ ተጠራ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ሁሉም እያንዳንዱ የወደረኛውን ራስ ያዘ፥ ሰይፉንም በወደረኛው ጎን ሻጠ፥ ተያይዘውም ወደቁ። የዚያም ስፍራ ስም የስለታም ሰይፍ እርሻ ተብሎ ተጠራ፥ እርሱም በገባዖን ነው። 参见章节 |