Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 19:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እርሱም የይሁዳን ሰዎች ልብ ሁሉ እንደ አንድ ሰው ልብ አድርጎ ማረከው፤ እነርሱም “አንተም ሰዎችህም ሁሉ ተመለሱ” ብለው ወደ ንጉሡ ላኩበት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 አማሳይንም፥ ‘አንተስ የዐጥንቴ ፍላጭ፥ የሥጋዬ ቁራጭ አይደለህምን? ከአሁን ጀምሮ እስከ ሕይወትህ ፍጻሜ በኢዮአብ ምትክ የሠራዊቴ አዛዥ ባላደርግህ፥ እግዚአብሔር ክፉ ያድርግብኝ፥ ከዚህ የባሰም ያምጣብኝ’ ብላችሁ ንገሩት።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የዳዊት አነጋገር የይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ለእርሱ ታማኞች እንዲሆኑ አደረጋቸው፤ ስለዚህም ከመኳንንቱ ሁሉ ጋር ተመልሶ እንዲመጣ ላኩበት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የይ​ሁ​ዳ​ንም ሰዎች ሁሉ ልብ እንደ አንድ ሰው ልብ አድ​ርጎ አዘ​ነ​በለ፤ ወደ ንጉ​ሡም፥ “አን​ተና ብላ​ቴ​ኖ​ችህ፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህም ሁሉ ተመ​ለሱ” ብለው ላኩ​በት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የይሁዳንም ሰዎች ሁሉ ልብ እንደ አንድ ሰው ልብ አድርጎ አዘነበለ፥ ወደ ንጉሡም ልከው፦ አንተ ከባሪያዎችህ ሁሉ ጋር ተመለስ አሉት።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 19:14
8 交叉引用  

አቤሴሎምም በኢዮአብ ምትክ አሜሳይን በሰራዊቱ ላይ ሾመ፤ አሜሳይ የእስማኤላዊው የዮቴር ልጅ ነበረ፤ ዮቴርም የኢዮአብን እናት፣ የጽሩያን እኅት፣ የናዖስን ልጅ አቢግያን አግብቶ ነበር።


ከዚያም ንጉሡ አሜሳይን፣ “የይሁዳ ሰዎች ሁሉ በሦስት ቀን ውስጥ፣ ወደ እኔ እንዲመጡ ጥራልኝ፤ አንተ ራስህም ተገኝ” አለው።


“በሕዝቤ ከተቃጣብኝ አደጋ አዳንኸኝ፤ የመንግሥታትም ራስ አደረግኸኝ። የማላውቀውም ሕዝብ ተገዛልኝ፤


እግዚአብሔር ለዳዊት በመሐላ የሰጠውን ተስፋ እዳር እንዲደርስ ሳላደርግ ብቀር እግዚአብሔር በአበኔር ላይ ክፉ ያድርግበት፤ ከዚያ የባሰም ያምጣበት፤


የእስራኤል ነገዶች በሙሉ ወደ ኬብሮን ወደ ዳዊት መጥተው እንዲህ አሉ፤ “እነሆ፤ እኛ የዐጥንትህ ፍላጭ፣ የሥጋህ ቍራጭ ነን፤


ያመኑትም ሁሉ በአንድ ልብና በአንድ ሐሳብ ተስማምተው ነበር፤ ያላቸውም ሁሉ የጋራ ነበር እንጂ የራሱ የሆነውን ሀብት እንኳ እንደ ግሉ የሚቈጥር ማንም አልነበረም።


ከዚያም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉ እንዲሁም በገለዓድ ምድር የሚገኙ እስራኤላውያን ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው ወጡ፤ በምጽጳም በእግዚአብሔር ፊት ተሰበሰቡ።


跟着我们:

广告


广告