2 ሳሙኤል 15:31 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም31 በዚህ ጊዜ፣ “ከአቤሴሎም ጋራ ካሤሩት መካከል አንዱ አኪጦፌል ነው” ብለው ለዳዊት ነገሩት። ስለዚህ ዳዊት፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህን የአኪጦፌልን ምክር ወደ ከንቱነት ለውጠው” ብሎ ጸለየ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)31 በዚህ ጊዜ፥ “ከአቤሴሎም ጋር ካሤሩት መካከል አንዱ አኪጦፌል ነው” ብለው ለዳዊት ነገሩት። ዳዊትም፥ “ጌታ ሆይ! እባክህን የአኪጦፌልን ምክር ወደ ከንቱነት ለውጠው” ሲል ጸለየ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም31 ዳዊት፥ አኪጦፌል ከአቤሴሎም ጋር በዐመፅ መተባበሩን በሰማ ጊዜ “እግዚአብሔር ሆይ! የአኪጦፌልን ምክር ወደ ከንቱነት እንድትለውጥበት እለምንሃለሁ!” ሲል ጸለየ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)31 አኪጦፌል ከአቤሴሎም ጋር በሴራ አንድ ነው ብለው ለዳዊት ነገሩት፤ ዳዊትም፥ “አቤቱ የአኪጦፌልን ምክር ለውጥ” አለ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)31 አኪጦፌል ከአቤሴሎም ጋር በሴራ አንድ ነው ብለው ለዳዊት ነገሩት፥ ዳዊትም፦ አቤቱ፥ የአኪጦፌልን ምክር ስንፍና አድርገህ እንድትለውጥ እለምንሃለሁ አለ። 参见章节 |