2 ሳሙኤል 15:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ዳዊትም ኢታይን፣ “በል እንግዲያው ቅደምና ሂድ” አለው። ስለዚህ ጋታዊው ኢታይን ሰዎቹን ሁሉና ዐብረውት የነበሩትን ቤተ ሰቦቹን ይዞ ሄደ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ዳዊትም ኢታይን፥ “እንግዲያውስ ቅደምና ሂድ” አለው። ስለዚህ ጌታዊው ኢታይ ሰዎቹን ሁሉና አብረውት የነበሩትን ቤተሰቦቹን ይዞ ሄደ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ዳዊትም “መልካም ነው! እንግዲህ ጒዞህን ቀጥል!” አለው፤ ስለዚህም ኢታይ ከወታደሮቹ ሁሉና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ጒዞውን ቀጠለ፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ንጉሡም ኤቲን፥ “ና ከእኔ ጋር ተሻገር” አለው፤ ጌታዊው ኤቲና ንጉሡም፥ አገልጋዮቹም፥ ከእርሱም ጋር የነበሩት ሕዝቡ ሁሉ ተሻገሩ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ዳዊትም ኢታይን፦ ሂድ ተሻገር አለው፥ የጌት ሰው ኢታይና ሰዎቹም ሁሉ፥ ከእርሱም ጋር የነበሩት ሕፃናት ሁሉ ተሻገሩ። 参见章节 |