Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 12:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ናታን ወደ ቤቱ ከሄደ በኋላ፣ የኦርዮ ሚስት ለዳዊት የወለደችለትን ሕፃን እግዚአብሔር ከባድ ሕመም ላይ ጣለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ናታን ወደ ቤቱ ከሄደ በኋላ፥ የኦርዮን ሚስት ለዳዊት የወለደችለትን ሕፃን ጌታ ከባድ ሕመም ላይ ጣለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ከዚህ በኋላ ናታን ወደ ቤቱ ሄደ። የኦርዮ ሚስት ለዳዊት የወለደችለትን ልጅ እግዚአብሔር በከባድ ሕመም ቀሠፈው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ናታ​ንም ወደ ቤቱ ተመ​ለሰ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የኦ​ርዮ ሚስት ለዳ​ዊት የወ​ለ​ደ​ች​ውን ሕፃን ቀሠ​ፈው፤ እጅ​ግም ታምሞ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ናታንም ወደ ቤቱ ተመለሰ። እግዚአብሔርም የኦርዮ ሚስት ለዳዊት የወለደችውን ሕፃን ቀሠፈ፥ እጅግም ታምሞ ነበር።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 12:15
9 交叉引用  

ይህን በመፈጸምህ ግን፣ የእግዚአብሔር ጠላቶች እጅግ እንዲያቃልሉት ስላደረግህ፣ የተወለደልህ ልጅ ይሞታል።”


ዳዊት ስለ ሕፃኑ እግዚአብሔርን ለመነ፤ ጾመም፤ ከዚያም ወደ ክፍሉ ገብቶ በተከታታይ ሌሊቱን መሬት ላይ ተኝቶ ዐደረ።


እግዚአብሔርም ንጉሡን ቀሠፈው፤ እስከሚሞትበትም ቀን ድረስ ለምጽ ነበረበት፤ በተለየ ቤትም ይኖር ነበር። በዚያ ጊዜ ቤተ መንግሥቱን በኀላፊነት የሚመራውና የአገሩንም ሕዝብ የሚያስተዳድረው የንጉሡ ልጅ ኢዮአታም ነበር።


ኢዮርብዓም በአብያ ዘመን እንደ ገና ሊያንሰራራ አልቻለም፤ ከዚያም እግዚአብሔር ስለ ቀሠፈው ሞተ።


ፊትህን ስትሰውር፣ በድንጋጤ ይሞላሉ፤ እስትንፋሳቸውንም ስትወስድባቸው ይሞታሉ፤ ወደ ዐፈራቸውም ይመለሳሉ።


ሄሮድስም ለእግዚአብሔር ክብር ስላልሰጠ የጌታ መልአክ ወዲያው መታው፤ በትልም ተበልቶ ሞተ።


“እኔ ራሴ እርሱ እንደ ሆንሁ እዩ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እገድላለሁ፤ አድናለሁም፤ አቈስላለሁ፤ እፈውሳለሁም፤ ከእጄም የሚያስጥል ማንም የለም።


ዐሥር ቀን ያህል ካለፈ በኋላ፣ እግዚአብሔር ናባልን ቀሠፈው፤ እርሱም ሞተ።


ሕያው እግዚአብሔርን! እግዚአብሔር ራሱ ይቀሥፈዋል፤ ወይም ቀኑ ደርሶ ይሞታል፤ ወይም በጦርነት ይሞታል።


跟着我们:

广告


广告