2 ነገሥት 9:33 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም33 ኢዩም፣ “ወደ ታች ወርውሯት!” አለ፤ እነርሱም ወረወሯት፤ ፈረሶቹ ሲረጋግጧትም ደሟ በግንቡና በፈረሶቹ ላይ ተረጨ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)33 ኢዩም “ኤልዛቤልን ወደ ታች ወርውሩአት!” አላቸው፤ እነርሱም አንሥተው በወረወሩአት ጊዜ ደምዋ በግንቡና በፈረሶች ላይ ተረጨ፤ ኢዩም በሬሳዋ ላይ ፈረሶቹንና ሠረገላውን ነዳበት፤ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም33 ኢዩም “ኤልዛቤልን ወደታች ወርውሩአት!” አላቸው፤ እነርሱም አንሥተው በወረወሩአት ጊዜ ደምዋ በግንቡና በፈረሶች ላይ ተረጨ፤ ኢዩም በሬሳዋ ላይ ፈረሶቹንና ሠረገላውን ነዳበት፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)33 እርሱም፥ “ወደ ታች ወርውሩአት” አላቸው፤ ወረወሩአትም፥ ደምዋም በግንቡና በፈረሶች መግሪያ ላይ ተረጨ፥ ረገጡአትም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)33 እርሱም “ወደ ታች ወርውሩአት፤” አለ፤ ወረወሩአትም፤ ደምዋም በግንቡና በፈረሶቹ ላይ ተረጨ፤ ረገጡአትም። 参见章节 |