Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 9:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ስለዚህ ንጉሡ ሌላ ፈረሰኛ ላከ፤ ወደ እነርሱ ዘንድ እንደ ደረሰም፣ “ንጉሡ፣ ‘የመጣችሁት በሰላም ነውን?’ ይላል” አለው። ኢዩም “ስለ ሰላም መጨነቅ የአንተ ጕዳይ አይደለም! ይልቅስ ወደ ኋላ ዕለፍና ተከተለኝ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ሌላም መልእክተኛ ተልኮ ያንኑ ተመሳሳይ ጥያቄ ለኢዩ አቀረበለት፤ ኢዩም “አንተ ከሰላም ጋር ምን ግንኙነት አለህ? ይልቅስ ወደ ኋላ አልፈህ ተከተለኝ!” ሲል መለሰለት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ሌላም መልእክተኛ ተልኮ ያንኑ ተመሳሳይ ጥያቄ ለኢዩ አቀረበለት፤ ኢዩም “አንተ ከሰላም ጋር ምን ግንኙነት አለህ? ይልቅስ ወደ ኋላ አልፈህ ተከተለኝ!” ሲል መለሰለት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ፈረ​ሰኛ ሰደደ፤ ወደ እነ​ር​ሱም ደርሶ ንጉሡ እን​ዲህ ይላል፥ “ሰላም ነውን?” አላ​ቸው። ኢዩም፥ “አንተ ከሰ​ላም ጋር ምን አለህ? ወደ ኋላዬ ተመ​ል​ሰህ ተከ​ተ​ለኝ” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ሁለተኛም ፈረሰኛ ሰደደ፤ ወደ እነርሱም ደርሶ “ንጉሡ እንዲህ ይላል ‘ሰላም ነውን?’” አለ። ኢዩም “አንተ ከሰላም ጋር ምን አለህ? ወደ ኋላዬ አልፈህ ተከተለኝ፤” አለ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 9:19
5 交叉引用  

ኢዩ ወጥቶ የጦር አለቆች ወደሆኑት ጓደኞቹ እንደ ደረሰ፣ ከመካከላቸው አንዱ “ሁሉም ነገር ሰላም ነው? ይህ እብድ ወደ አንተ የመጣው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ኢዩም “ሰውየውንም ሆነ የሚናገረውን እናንተም ታውቃላችሁ” ሲል መለሰ።


በኢይዝራኤል ግንብ ማማ ላይ የቆመው ጠባቂ የኢዩ ወታደሮች መቅረባቸውን አይቶ፣ “ኧረ ወታደሮች መጡ” በማለት ጮኾ ተናገረ። ኢዮራምም፣ “አንድ ፈረሰኛ ተጠርቶ፤ እንዲገናኛቸው ላኩትና፣ ‘የመጣችሁት በሰላም ነውን?’ ብሎ ይጠይቅ” ሲል አዘዘ።


ፈረሰኛውም ኢዩን ለመገናኘት ጋልቦ ሄደና፣ “ንጉሡ፣ ‘የመጣችሁት በሰላም ነውን?’ ብሏል” አለው። ኢዩም፣ “ስለ ሰላም መጨነቅ የአንተ ጕዳይ አይደለም! ይልቅስ ወደ ኋላ ዕለፍና ተከተለኝ” አለው። ጠባቂውም፣ “መልእክተኛው ከእነርሱ ዘንድ ደርሷል፤ ነገር ግን ተመልሶ አልመጣም” ብሎ አሳወቀ።


ጠባቂው፣ “መልእክተኛው ከእነርሱ ዘንድ ደርሷል፤ ነገር ግን ይህም ተመልሶ አልመጣም፤ የወታደሮቹ መሪ ሠረገላ አነዳዱ ልክ እንደ ናሜሲ ልጅ እንደ ኢዩ አነዳድ ነው፤ ሲነዳም እንደ እብድ ነው” ሲል አሳወቀ።


“ለክፉዎች ሰላም የላቸውም” ይላል እግዚአብሔር።


跟着我们:

广告


广告