Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 7:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እንዲሁም የእግዚአብሔር ሰው ለንጉሡ፣ “ነገ በዚሁ ሰዓት በሰማርያ በር ላይ አንድ መስፈሪያ ዱቄት በአንድ ሰቅል፣ ሁለት መስፈሪያ ገብስም በአንድ ሰቅል ይሸጣል” ያለውም ተፈጸመ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በዚያን ጊዜ ኤልሳዕ ለንጉሡ “በነገው ዕለት በሰማርያ ከተማ ሦስት ኪሎ ምርጥ ስንዴ ወይም ስድስት ኪሎ ገብስ በአንድ ጥሬ ብር ይሸመታል” ብሎ ነግሮት ነበር፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በዚያን ጊዜ ኤልሳዕ ለንጉሡ “በነገው ዕለት በሰማርያ ከተማ ሦስት ኪሎ ምርጥ ስንዴ ወይም ስድስት ኪሎ ገብስ በአንድ ጥሬ ብር ይሸመታል” ብሎ ነግሮት ነበር፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ኤል​ሳ​ዕም ለን​ጉሡ፥ “ነገ በዚህ ጊዜ በሰ​ማ​ርያ በር ሁለት መስ​ፈ​ሪያ ገብስ በአ​ንድ ሰቅል፥ አንድ መስ​ፈ​ሪያ መል​ካም ዱቄ​ትም በአ​ንድ ሰቅል፥ ይሸ​መ​ታል” ብሎ እንደ ተና​ገ​ረው ነገር እን​ዲሁ ሆነ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 የእግዚአብሔርም ሰው ለንጉሡ “ነገ በዚህ ጊዜ በሰማርያ በር ሁለት መስፈሪያ ገብስ በአንድ ሰቅል፥ አንድም መስፈሪያ መልካም ዱቄት በአንድ ሰቅል ይሸመታል፤” ብሎ እንደ ተናገረው ነገር እንዲሁ ሆነ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 7:18
5 交叉引用  

ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? ጊዜው ሲደርስ እመለሳለሁ፤ ሣራም ልጅ ይኖራታል።”


በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ በቤቱ ተቀምጦ ነበር፤ ሽማግሌዎችም ዐብረውት ተቀምጠው ነበር። ንጉሡም መልእክተኛ ቀድሞት እንዲሄድ አደረገ። የተላከውም ሰው ከመድረሱ በፊት ኤልሳዕ ለሽማግሌዎቹ፣ “ይህ ነፍሰ ገዳይ ራሴን ለመቍረጥ ሰው መላኩን ታያላችሁ? እነሆ፤ አሁንም መልእክተኛው ሲደርስ በሩን ዘግታችሁ እንዳይገባ አድርጉ። የጌታው የእግሩ ኮቴ ከኋላው ይሰማ የለምን?” አላቸው።


የጦር አለቃው ለእግዚአብሔር ሰው፣ “እግዚአብሔር የሰማይን መስኮቶች ቢከፍት እንኳ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?” ብሎት ስለ ነበር፣ የእግዚአብሔር ሰው፣ “ይህን አንተው ራስህ ታያለህ፤ ከዚህ ግን አንዳች አትበላም” ሲል መልሶለት ነበር።


የባሪያዎቼን ቃል እፈጽማለሁ፤ የመልእክተኞቼን ምክር አጸናለሁ። “ኢየሩሳሌምን ‘የሰው መኖሪያ ትሆኛለሽ፣’ የይሁዳ ከተሞችንም፣ ‘ይታነጻሉ’፣ ፍርስራሻቸውን፣ ‘አድሳለሁ’ እላለሁ።


跟着我们:

广告


广告