Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 6:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ የእግዚአብሔር ሰው የነገረውን ቦታ አስቃኘ፤ ኤልሳዕም ንጉሡን እንደዚህ ካሉት ቦታዎች ራሱን እንዲጠብቅ ከአንድ ሁለት ጊዜ በላይ አስጠነቀቀው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ስለዚህም የእስራኤል ንጉሥ በዚያ የሚኖሩትን ወታደሮቹን ስላስጠነቀቃቸው ነቅተው ይጠባበቁ ነበር፤ ይህም ድርጊት ብዙ ጊዜ በተደጋጋሚ ተፈጸመ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ስለዚህም የእስራኤል ንጉሥ በዚያ የሚኖሩትን ወታደሮቹን ስላስጠነቀቃቸው ነቅተው ይጠባበቁ ነበር፤ ይህም ድርጊት ብዙ ጊዜ በተደጋጋሚ ተፈጸመ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ኤል​ሳዕ ወደ ነገ​ረው ስፍራ ላከ፤ አንድ ጊዜም ሳይ​ሆን፥ ሁለት ጊዜም ሳይ​ሆን በዚያ ራሱን አዳነ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የእስራኤልም ንጉሥ የእግዚአብሔር ሰው ወደ ነገረው ስፍራ ሰደደ፤ አንድ ጊዜም ሳይሆን፥ ሁለት ጊዜም ሳይሆን በዚያ ራሱን አዳነ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 6:10
17 交叉引用  

ስለዚህ አክዓብ የየአውራጃው አዛዥ የሆኑትን ሁለት መቶ ሠላሳ ሁለት ወጣት መኰንኖች ጠራ፤ ከዚያም የቀሩትን እስራኤላውያን ሰበሰበ፤ እነዚህም በአጠቃላይ ሰባት ሺሕ ነበሩ።


በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ ለሞት ባደረሰው ሕመም ታምሞ ነበር። የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ ሊጠይቀው ወርዶ አለቀሰለት፤ “ወየው አባቴን! ወየው አባቴን! ወየው የእስራኤል ሠረገሎችና ፈረሰኞች!” እያለም ጮኸ።


ኤልሳዕም ይህን አይቶ፣ “አባቴ አባቴ የእስራኤል ሠረገሎችና ፈረሰኞች!” ብሎ ጮኸ፤ ዳግመኛም ኤልያስን አላየውም፤ ከዚያም የገዛ ልብሱን ይዞ ከሁለት ቦታ ቀደደው።


ስለዚህ ንዕማን ወረደ፤ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ነገረውም በዮርዳኖስ ሰባት ጊዜ ብቅ ጥልቅ አለ፤ ሥጋውም እንደ ትንሽ ልጅ ሥጋ ሆነ፤ ነጻም።


ይህም የሶርያን ንጉሥ እጅግ ስላበሳጨው፣ የጦር አለቆቹን ጠርቶ፣ “ከመካከላችን ከእስራኤል ንጉሥ ጋራ የተወዳጀ እንዳለ ለምን አትነግሩኝም?” ሲል ጠየቃቸው።


የእግዚአብሔርም ሰው፣ “ሶርያውያን በዚያ ታች ወርደዋልና በዚያ በኩል እንዳታልፍ ተጠንቀቅ” ሲል ለእስራኤል ንጉሥ ላከበት።


በማግስቱም ጧት በማለዳ ተነሥተው ወደ ቴቁሔ ምድረ በዳ ሄዱ። መንገድ እንደ ጀመሩም ኢዮሣፍጥ ቆሞ፣ “ይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ፣ ስሙኝ! በአምላካችሁ በእግዚአብሔር እመኑ፤ ትጸኑማላችሁ። በነቢያቱም እመኑ፤ ይሳካላችሁማል” አላቸው።


አስተዋይ ክፉን አይቶ ራሱን ይሸሽጋል፤ አላዋቂዎች ግን በዚያው ይቀጥላሉ፤ ይቀጡበታልም።


እግዚአብሔር ስውር ዕቅዳቸውን ገለጠልኝ፤ እኔም ዐወቅሁ፤ በዚያ ጊዜ ሥራቸውን አሳይቶኝ ነበርና።


እግዚአብሔርም ወደ ሄሮድስ እንዳይመለሱ በሕልም ባስጠነቀቃቸው መሠረት፣ መንገድ አሳብረው ወደ አገራቸው ተመለሱ።


ብዙ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ወደሚያጠምቅበት ስፍራ ሲመጡ ባየ ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ የእፉኝት ልጆች! ከሚመጣው ቍጣ እንድታመልጡ ማን መከራችሁ?


‘ጳውሎስ ሆይ፤ አትፍራ፤ በቄሳር ፊት መቆም ይገባሃል፤ ከአንተ ጋራ የሚጓዙትንም ሰዎች ሕይወት እግዚአብሔር አትርፎልሃል’ አለኝ።


ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር እግዚአብሔር ባስጠነቀቀው ጊዜ፣ እግዚአብሔርን ፈርቶ ቤተ ሰዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት ሠራ፤ በእምነቱ ዓለምን ኰነነ፤ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።


跟着我们:

广告


广告