Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 19:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 በእኔ ላይ በቍጣ ስለ ተነሣሣህ፣ እብሪትህም ወደ ጆሮዬ ስለ ደረሰ፣ ስናጋዬን በአፍንጫህ አደርጋለሁ፤ ልጓሜን በአፍህ አስገባለሁ፤ በመጣህበትም መንገድ እንድትመለስ አደርግሃለሁ።’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 በእኔ ላይ ያለው ተቃውሞህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአል፤ በአፍንጫህ ስናጋ፥ በአፍህ ልጓም አድርጌ፥ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 በእኔ ላይ ያለው ተቃውሞህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአል፤ በአፍንጫህ ስናጋ፥ በአፍህ ልጓም አድርጌ፥ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ቍጣ​ህና ትዕ​ቢ​ትህ ወደ ጆሮዬ ደር​ሶ​አ​ልና ስለ​ዚህ ስና​ጋ​ዬን በአ​ፍ​ን​ጫህ፥ ልጓ​ሜ​ንም በከ​ን​ፈ​ርህ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በመ​ጣ​ህ​በት መን​ገ​ድም እመ​ል​ስ​ሃ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ቍጣህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአልና ስለዚህ ስናጋዬን በአፍንጫህ፥ ልጓሜንም በከንፈርህ አደርጋለሁ፤ በመጣህበትም መንገድ እመልስሃለሁ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 19:28
25 交叉引用  

በመጣበት መንገድ ይመለሳል፤ ወደዚህች ከተማም አይገባም’ ይላል እግዚአብሔር።


እነሆ፤ በላዩ መንፈስን እሰድዳለሁ፤ ወሬም ሰምቶ ወደ አገሩ ይመለሳል፤ በገዛ አገሩም በሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ።’ ”


የደረበውን ልብስ ማን ሊያወልቅ ይችላል? ማንስ ሊለጕመው ወደ መንጋጋው ይቀርባል?


መሰነጊያ በአፍንጫው ልታስገባ፣ ወይም ጕንጩን በሜንጦ ልትበሳ ትችላለህን?


በልባብና በልጓም ካልተገሩ በቀር፣ ወደ አንተ እንደማይቀርቡት፣ ማስተዋል እንደሌላቸው፣ እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትሁኑ።


ሕዝቦች በዐመፅ ተነሡ፤ መንግሥታትም ወደቁ፤ ድምፁን ከፍ አድርጎ አሰማ፤ ምድርም ቀለጠች።


አንተ የባሕሮችን ማስገምገም፣ የማዕበላቸውን ፉጨት፣ የሕዝቦችንም ሁከት ጸጥ ታደርጋለህ።


እግዚአብሔር ሆይ፤ በመዓትህ ተነሥ፤ በቍጣ በተነሡብኝ ላይ ተነሥ፤ አምላኬ ሆይ፤ ንቃ፤ ትእዛዝም አስተላልፍ!


የባላጋራዎችህን ድንፋታ፣ ዘወትር የሚነሣውን የጠላቶችህን ፉከራ አትርሳ።


ጠላቶችህ በመገናኛ ስፍራህ መካከል ደነፉ፤ አርማቸውንም ምልክት አድርገው በዚያ አቆሙ።


ጠላቶችህ እንዴት እንደ ተነሣሡ፣ ባላንጣዎችህም እንዴት ራሳቸውን ቀና ቀና እንዳደረጉ ተመልከት።


እስትንፋሱ እንደሚጠራርግ፣ እስከ ዐንገት እንደሚደርስም የውሃ ሙላት ነው፤ መንግሥታትን በጥፋት ወንፊት ያበጥራቸዋል፤ በሕዝቦችም መንጋጋ፣ መንገድ የሚያስት ልጓም ያስገባል።


በስናግም በመጐተት ቀፎ ውስጥ ከትተው፣ ወደ ባቢሎን ንጉሥ አመጡት፤ ድምፁ በእስራኤል ተራሮች ላይ፣ ዳግመኛ እንዳይሰማ፣ በእስር ቤት አኖሩት።


ነገር ግን በመንጋጋህ መንጠቆ አስገባለሁ፤ የወንዞችህን ዓሦች ከቅርፊትህ ጋራ አጣብቃለሁ፤ ቅርፊትህ ላይ ከተጣበቁት ዓሦች ሁሉ ጋራ፣ ከወንዞችህ ጐትቼ አወጣሃለሁ።


በእኔ ላይ ታብየሃል፤ በድፍረትም በእኔ ላይ ተናግረሃል፤ እኔም ሰምቼዋለሁ።


ወደ ኋላ እመልስሃለሁ፤ መንጋጋህ ውስጥ መንጠቆ አስገብቼ ከመላው ሰራዊትህ ጋራ፣ ፈረሶችህን፣ ፈረሰኞችህን ከነሙሉ ትጥቃቸው፣ ትልቅና ትንሽ ሰይፍ የያዙትን ሁሉ፣ ሰይፋቸውንም የወለወሉትን ሁሉ አስወጣለሁ።


ጌታ እግዚአብሔር በቅድስናው እንዲህ ሲል ምሏል፤ “እነሆ፤ በመንጠቆ ተይዛችሁ የምትወሰዱበት ትሩፋናችሁ እንኳ፣ በዓሣ መንጠቆ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል።


ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራን ግን በቍጣ ተሞሉ፤ በኢየሱስ ላይ ምን ማድረግ እንዳለባቸውም እርስ በርስ ተወያዩ።


“ዓለም ቢጠላችሁ፣ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ ዕወቁ።


“እናንተ ልባችሁና ጆሯችሁ ያልተገረዘ! ዐንገተ ደንዳኖች ልክ እንደ አባቶቻችሁ መንፈስ ቅዱስን ሁልጊዜ ትቃወማላችሁ።


跟着我们:

广告


广告