Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 1:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ንጉሡንም፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ለመሆኑ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ስለ ራስህ ለመጠየቅ መልእክተኞች የላክኸው በእስራኤል አምላክ ስለሌለ ነውን? ይህን በማድረግህም ከተኛህበት ዐልጋ ፈጽሞ አትነሣም፤ በርግጥ ትሞታለህ’ ” ብሎ ነገረው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 “እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ ‘በእስራኤል አምላክ እንደሌለ በመቁጠር፥ የዔክሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን እንዲጠይቁልህ መልእክተኞች በመላክህ ምክንያት ትሞታለህ እንጂ አትድንም!’” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 “እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ ‘በእስራኤል አምላክ እንደሌለ በመቊጠር፥ የዔክሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን እንዲጠይቁልህ መልእክተኞች በመላክህ ምክንያት ትሞታለህ እንጂ አትድንም!’ ” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ኤል​ያ​ስም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ትጠ​ይቅ ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ለምን ላክህ? በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አም​ላክ ስለ​ሌለ ነውን? እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ ከወ​ጣ​ህ​በት አልጋ አት​ወ​ር​ድም” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ኤልያስም “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ትጠይቅ ዘንድ መልእክተኞችን ልከሃልና ትሞታለህ እንጂ ከወጣህበት አልጋ አትወርድም’” አለው።

参见章节 复制




2 ነገሥት 1:16
13 交叉引用  

ሚክያስም፣ “አንተ በደኅና ከተመለስክማ እግዚአብሔር በእኔ አልተናገረም ማለት ነው!” አለ፤ ቀጥሎም፣ “እናንተ ሰዎች ሁላችሁ ስሙኝ” አለ።


እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “አንድ ሰው ሊገናኘን መጥቶ፣ ‘ወደ ላካችሁ ንጉሥ ተመልሳችሁ ሂዱና፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ለመጠየቅ ሰዎች የምትልከው በእስራኤል አምላክ ስለሌለ ነውን? ስለዚህ ከተኛህበት ዐልጋ አትነሣም፤ በርግጥ ትሞታለህ።” ’ ”


ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ፤ ሊሞት ተቃርቦ ነበር። የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስም ወደ እርሱ መጥቶ፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ከሕመምህ አትድንም፤ ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል’ ” አለው።


ስለዚህ ግያዝ ንዕማንን ተከተለው፤ ንዕማንም ግያዝ እየሮጠ ወደ እርሱ መምጣቱን ባየ ጊዜ፣ ሊገናኘው ከሠረገላው ወርዶ፣ “ምነው፤ በደኅና መጣህን?” ሲል ጠየቀው።


ኤልሳዕም፣ “ሂድና፣ ‘መዳኑንስ በርግጥ ትድናለህ’ በለው፤ ነገር ግን እንደሚሞት እግዚአብሔር ገልጾልኛል” ሲል መለሰለት።


ንጉሡም አዛሄልን፣ “ገጸ በረከት ይዘህ ሂድና የእግዚአብሔርን ሰው ተገናኘው። በርሱም አማካይነት፣ ‘ከዚህ በሽታ እድናለሁን?’ ብለህ እግዚአብሔርን ጠይቅ” አለው።


“ወደ ቤቴ አልገባም፤ ዐልጋዬም ላይ አልወጣም፤


እውነተኛ ጻድቅ ሕይወትን ያገኛል፤ ክፋትን የሚከተል ግን ወደ ሞቱ ይጓዛል።


ስለዚህ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ማንኛውም እስራኤላዊ ጣዖትን በልቡ አኑሮ፣ ክፋቱንም የማሰናከያ ድንጋይ አድርጎ በፊቱ በማስቀመጥ ወደ ነቢይ ቢመጣ፣ እኔ እግዚአብሔር እንደ ጣዖቱ ብዛት እመልስለታለሁ።


跟着我们:

广告


广告