Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ቆሮንቶስ 12:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ቲቶ ወደ እናንተ እንዲመጣ ለመንሁት፤ ወንድማችንንም ከርሱ ጋራ ላክሁት። ቲቶ በዘበዛችሁን? ከርሱ ጋራ በአንድ መንፈስ አልተመላለስንምን? አካሄዳችንስ አንድ አልነበረምን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ቲቶን ገፋፋሁት፤ ከእርሱም ጋር ወንድሙን ላክሁት፤ ቲቶስ ለራሱ ጥቅም አውሏችኋልን? በአንድ መንፈስ አልተመላለስንምን? አንድ ዓይነት እርምጃስ አልወሰድንምን?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ቲቶ ወደ እናንተ እንዲመጣ ለመንኩት፤ ያንን ወንድማችንንም ከእርሱ ጋር ላክሁት፤ ታዲያ፥ ቲቶስ ተጠቀመባችሁን? እኔና እርሱ ያገለገልናችሁ በአንድ መንፈስ አልነበረምን? አካሄዳችንስ አንድ አልነበረምን?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እነሆ ቲቶን ማለ​ድ​ሁት፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ሌላ​ውን ወን​ድ​ማ​ች​ንን ላክ​ሁት፤ በውኑ ቲቶ የበ​ደ​ላ​ችሁ በደል አለን? በእ​ርሱ በአ​ደ​ረው መን​ፈስ የም​ን​መ​ላ​ለስ፥ እር​ሱም የሄ​ደ​በ​ትን ፍለጋ የም​ን​ከ​ተል አይ​ደ​ለ​ን​ምን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ቲቶን መከርሁት ከእርሱም ጋር ወንድሙን ላክሁት፤ ቲቶስ አታለላችሁን? በአንድ መንፈስ አልተመላለስንምን? በአንድ ፍለጋስ አልተመላለስንም?

参见章节 复制




2 ቆሮንቶስ 12:18
13 交叉引用  

ከዚህም በላይ በይሁዳ ምድር አገረ ገዥ ሆኜ ከተሾምሁበት፣ ከአርጤክስስ ሃያኛ ዓመት ጀምሮ እስከ ሠላሳ ሁለተኛው ዘመነ መንግሥቱ ድረስ፣ ለዐሥራ ሁለት ዓመት እኔም ሆንሁ ወንድሞቼ ለአንድ አገረ ገዥ የተመደበውን ምግብ ተቀብለን አልበላንም።


ሙሴም በጣም ተቈጣ፤ እግዚአብሔርንም “ቍርባናቸውን አትቀበል፤ እኔ ከእነዚህ ሰዎች የወሰድሁት አንድ አህያ እንኳ የለም፤ አንዳቸውንም አልበደልሁም” አለ።


እርሱ ለተገረዙትም አባት ነው፤ መገረዝ ብቻ ሳይሆን፣ አባታችን አብርሃም ከመገረዙ በፊት የነበረውን የእምነቱን ፈለግ ለሚከተሉ ሁሉ ነው።


ለመሆኑ የምትፈልጉት የቱን ነው? በትር ይዤ ልምጣ ወይስ በፍቅርና በገርነት መንፈስ?


ልባችሁን አስፉልን፤ እኛ ማንንም አልበደልንም፤ ማንንም ወደ ብልሹነት አልመራንም፤ ማንንም አላታለልንም።


ይሁን እንጂ ሐዘንተኞችን የሚያጽናና አምላክ በቲቶ መምጣት አጽናናን።


ስለዚህ ቲቶ፣ በእናንተ መካከል ቀደም ሲል የጀመረውን የልግስና ሥራ ከፍጻሜ እንዲያደርስ ለምነነው ነበር።


የተጠራችሁትም ለዚሁ ነው፤ ምክንያቱም ክርስቶስ ስለ እናንተ መከራን የተቀበለው የርሱን ፈለግ እንድትከተሉ ምሳሌን ሊተውላችሁ ነው።


跟着我们:

广告


广告