2 ዜና መዋዕል 9:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም20 ንጉሥ ሰሎሞን የሚጠጣባቸው ዕቃዎች በሙሉ ከወርቅ የተሠሩ ነበሩ፤ “የሊባኖስ ደን” ተብሎ በሚጠራው ቤተ መንግሥት ውስጥ የነበሩትም ዕቃዎች ሁሉ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበሩ፤ በሰሎሞን ዘመን ብር ዋጋ እንደሌለው ስለሚቈጠር ከብር የተሠራ አንድም ነገር አልነበረም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 ንጉሡም ሰሎሞን የሚጠጣበት ዕቃ ሁሉ የወርቅ ነበረ፥ የሊባኖስ ዱር በተባለውም ቤቱ የነበረው ዕቃ ሁሉ ንጹሕ ወርቅ ነበረ፤ በሰሎሞን ዘመን ብር እንደ ምንም አይቈጠርም ነበር። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 ንጉሥ ሰሎሞን የሚጠጣባቸው ዋንጫዎችና “የሊባኖስ ደን” ተብሎ በሚጠራው አዳራሽ ውስጥ የሚገኙት ዕቃዎች ሁሉ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበሩ፤ በሰሎሞን ዘመነ መንግሥት ብር ከመብዛቱ የተነሣ ዋጋ እንዳለው ሆኖ አይቈጠርም ነበር። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ንጉሡም ሰሎሞን የሚጠጣበት ዕቃ ሁሉ የወርቅ ነበረ፤ የሊባኖስ ዱር በተባለውም ቤቱ የሚገለገልበት ዕቃ ሁሉ ጥሩ ወርቅ ነበረ፤ በሰሎሞንም ዘመን ብር ከቶ አይቈጠርም ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ንጉሡም ሰሎሞን የሚጠጣበት ዕቃ ሁሉ የወርቅ ነበረ፤ የሊባኖስ ዱር በተባለውም ቤቱ የነበረው ዕቃ ሁሉ ጥሩ ወርቅ ነበረ፤ በሰሎሞን ዘመን ብር ከቶ አይቈጠርም ነበር። 参见章节 |