Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 9:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ይህም ከታላላቅና ከተራ ነጋዴዎች ከሚገባው ቀረጥ ሌላ ነበር። መላው የዐረብ ነገሥታትና አገረ ገዦች ለሰሎሞን ወርቅና ብር ያመጡለት ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ነጋድራሶችና ነጋዴዎች የሚያመጡትን ወርቅ የሚጨምር አልነበረም፤ የዓረብም ነገሥታት ሁሉ የምድሩም ሹማምንት ወርቅና ብር ወደ ሰሎሞን ያመጡ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ይህም ነጋዴዎች ከሚከፍሉት ቀረጥ፥ እንዲሁም ከዐረብ ነገሥታትና ከእስራኤል ክፍላተ ሀገር አስተዳዳሪዎች ከሚገባለት ግብር ሌላ ተጨማሪ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ነጋ​ድ​ራ​ሶ​ችና ነጋ​ዴ​ዎች ከሚ​ያ​መ​ጡት ሌላ የዓ​ረብ ነገ​ሥ​ታት ሁሉ፥ የም​ድ​ሩም ሹሞች ወደ ንጉሡ ሰሎ​ሞን ወር​ቅና ብር ያመጡ ነበር

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የዓረብም ነገሥታት ሁሉ የምድሩም ሹማምት ወርቅና ብር ወደ ሰሎሞን ያመጡ ነበር።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 9:14
7 交叉引用  

ይህም ከታላላቅና ከተራ ነጋዴዎች ከሚገባው ቀረጥ፣ መላው የዐረብ ነገሥታት ከሚያስገቡትና አገረ ገዦች ከሚሰበስቡት ግብር ሌላ ነበር።


ከፍልስጥኤማውያንም አንዳንዶቹ ለኢዮሣፍጥ እጅ መንሻ አመጡለት፤ ጥሬ ብርም ገበሩለት፤ ዐረቦችም ሰባት ሺሕ ሰባት መቶ አውራ በግና ሰባት ሺሕ ሰባት መቶ አውራ ፍየል መንጋ አመጡለት።


ንጉሥ ሰሎሞን ሁለት መቶ ከጥፍጥፍ ወርቅ ትላልቅ ጋሻዎችን አበጀ፤ በእያንዳንዱም ጋሻ የገባው ስድስት መቶ ሰቅል ጥፍጥፍ ወርቅ ነበር።


በኢየሩሳሌም ስላለው ቤተ መቅደስህ፣ ነገሥታት እጅ መንሻ ያመጡልሃል።


በሸንበቆ መካከል ያሉትን አራዊት፣ በሕዝቡ ጥጆች መካከል ያለውንም የኰርማ መንጋ ገሥጽ፤ ብር ይገብር ዘንድም ይንበርከክ፤ ጦርነትን የሚወድዱ ሕዝቦችንም በትናቸው።


የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት፣ ግብር ያመጡለታል፤ የዐረብና የሳባ ነገሥታት፣ እጅ መንሻ ያቀርባሉ።


የዐረብ ነገሥታትን ሁሉ፣ በምድረ በዳ የሚኖሩትን የድብልቅ ሕዝብ ነገሥታት ሁሉ፣


跟着我们:

广告


广告