Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 8:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ኪራምም ባሕሩን በሚያውቁት በራሱ መኰንኖች የሚታዘዙ መርከቦችን ላከለት፤ እነዚህም ከሰሎሞን ሰዎች ጋራ በመሆን ወደ ኦፊር ተጓዙ፤ ከዚያም አራት መቶ ዐምሳ መክሊት ወርቅ ወደ ንጉሥ ሰሎሞን አመጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ኪራምም መርከቦችንና የባሕርን ነገር የሚያውቁትን መርከበኞች በባርያዎቹ እጅ ላከለት፤ እነርሱም ከሰሎሞን ባርያዎች ጋር ወደ ኦፊር መጡ፥ ከዚያም አራት መቶ ኀምሳ መክሊት ወርቅ ወስደው ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን አመጡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ንጉሥ ኪራም በሠለጠኑ መርከበኞች የሚነዱና በራሱ መኰንኖች የሚመሩ መርከቦችን ለሰሎሞን ልኮለት ነበር፤ እነርሱም ከሰሎሞን መኰንኖች ጋር በመሆን ወደ ኦፊር ምድር መጡ፤ ከዚያም ከዐሥራ አምስት ሺህ ኪሎ የሚበልጥ ወርቅ ለሰሎሞን ይዘውለት መጡ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ኪራ​ምም መር​ከ​ቦ​ች​ንና የባ​ሕ​ርን ነገር የሚ​ያ​ው​ቁ​ትን መር​ከ​በ​ኞች በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ እጅ ላከ​ለት፤ እነ​ር​ሱም ከሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮች ጋር ወደ ሴፌር መጡ፤ ከዚ​ያም አራት መቶ አምሳ መክ​ሊት ወርቅ ወስ​ደው ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎ​ሞን አመጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ኪራምም መርከቦችንና የባሕርን ነገር የሚያውቁትን መርከበኞች በባሪያዎቹ እጅ ሰደደለት፤ እነርሱም ከሰሎሞን ባሪያዎች ጋር ወደ ኦፊር መጡ፤ ከዚያም አራት መቶ አምሳ መክሊት ወርቅ ወስደው ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን አመጡ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 8:18
6 交叉引用  

ንጉሡ ከኪራም መርከቦች ጋራ ዐብረው በባሕር ላይ የሚጓዙ የተርሴስ የንግድ መርከቦች ነበሩት። እነዚህም በየሦስት ዓመቱ አንድ ጊዜ ወርቅ፣ ብርና የዝሆን ጥርስ፣ ጦጣዎችና ዝንጀሮዎች ያመጡ ነበር።


የኪራም ሰዎችና የሰሎሞን ሰዎች ከኦፊር ወርቅ እንደዚሁም ሰንደልና የከበሩ ድንጋዮች አመጡ።


ለሰሎሞን በየዓመቱ የሚገባለት ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት መክሊት የሚመዝን ወርቅ ነበር።


ንጉሡ በኪራም ሰዎች የሚነዱ የተርሴስ መርከቦች ነበሩት፤ እነዚህም በየሦስት ዓመቱ አንድ ጊዜ ወርቅ፣ ብርና፣ የዝሆን ጥርስ፣ ጦጣዎችና ዝንጀሮዎች እየያዙ ይመለሱ ነበር።


ለራሴም ብርንና ወርቅን፣ የነገሥታትና የአውራጃዎችን ሀብት አካበትሁ፤ ወንድና ሴት አዝማሪዎች፣ የሰው መደሰቻ የሆኑ ቅምጦች ነበሩኝ።


跟着我们:

广告


广告