Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 7:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በዚያ ጊዜም ሰሎሞን ዐብረውት ከነበሩት ከእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ጋራ ለሰባት ቀን በዓሉን አከበረ፤ ሕዝቡም ከሐማት መግቢያ እስከ ግብጽ ወንዝ ድረስ ካለው ምድር የመጣ እጅግ ታላቅ ጉባኤ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ሰሎሞንም ከእርሱም ጋር እጅግ ታላቅ ጉባኤ የሆኑ፥ ከሐማት መግቢያ ጀምሮ እስከ ግብጽ ወንዝ ድረስ ያሉ እስራኤል ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ ሰባት ቀን በዓል አደረጉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በዚያም በቤተ መቅደሱ ሰሎሞንና እስራኤላውያን ሁሉ ሰባት ቀን ሙሉ የዳስ በዓል አክብረው ሰነበቱ፤ በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ አንሥቶ በስተ ደቡብ እስከ ግብጽ ሸለቆ ድረስ ካለው ምድር ሁሉ የመጣው ሕዝብ እጅግ ብዙ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ሰሎ​ሞ​ንም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እጅግ ታላቅ ጉባኤ የሆኑ ከኤ​ማት መግ​ቢያ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ያሉ እስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ በዚያ ጊዜ ሰባት ቀን በዓል አደ​ረጉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ሰሎሞንም ከእርሱም ጋር እጅግ ታላቅ ጉባኤ የሆኑ፥ ከሐማት መግቢያ ጀምሮ እስከ ግብጽ ወንዝ ድረስ ያሉ እስራኤል ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ ሰባት ቀን በዓል አደረጉ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 7:8
19 交叉引用  

በዚያ ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ሲል ኪዳን ገባለት፤ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ታላቁ የኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ፤


በዓሉ በሚከበርበት ኤታኒም በተባለው በሰባተኛው ወር፣ የእስራኤል ወንዶች ሁሉ ንጉሥ ሰሎሞን ወዳለበት ተሰበሰቡ።


በዚያ ጊዜም ሰሎሞን ዐብረውት ከነበሩት ከእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ጋራ፣ ማለትም ከሐማት መተላለፊያ እስከ ግብጽ ደረቅ ወንዝ ካለው ምድር ከተሰበሰበው ታላቅ ጉባኤ ጋራ በዓሉን አከበረ። እነርሱም ሰባት ቀን፣ በተጨማሪም ሌላ ሰባት ቀን በድምሩ ዐሥራ አራት ቀን በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት በዓሉን አከበሩ።


በሁለተኛው ወር የቂጣን በዓል ለማክበር እጅግ ብዙ ሕዝብ በኢየሩሳሌም ተሰበሰበ።


ከእስራኤል ንጉሥ ከዳዊት ልጅ ከሰሎሞን ጊዜ አንሥቶ በኢየሩሳሌም እንዲህ ያለ በዓል ተደርጎ ስለማያውቅ፣ በኢየሩሳሌም ታላቅ ደስታ ሆነ።


የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ የሰባተኛው ወር በዓል በሚከበርበት ጊዜ፣ በንጉሡ ፊት ተሰበሰቡ።


“ ‘በሰባተኛው ወር በዐሥራ ዐምስተኛው ቀን በሚጀመረው በሰባቱ ቀን በዓል፣ ለኀጢአት መሥዋዕት፣ ለሚቃጠል መሥዋዕት፣ ለእህል ቍርባንና ለዘይቱም እንዲሁ ያቅርብ።


በምዕራቡ በኩል ወሰኑ ከሐማት መግቢያ ፊት ለፊት እስካለው ቦታ ድረስ ታላቁ ባሕር ይሆናል፤ ይህም የምዕራቡ ወሰን ይሆናል።


የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፤ እነሆ፤ እኔ ከሐማት መግቢያ እስከ ዓረባ ሸለቆ ድረስ፣ የሚያስጨንቃችሁን ሕዝብ፣ በእናንተ ላይ አስነሣለሁ።”


የአይሁድ የዳስ በዓል በተቃረበ ጊዜ ግን፣


跟着我们:

广告


广告